የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በዛሬው ዕለት የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር አካሄዱ፡፡
በአፍሪካ ልህቀት ማዕከል በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርኃ ግብር የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ የፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በማዕከሉ ውስጥ Root Trainer Tray በሚባል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የፈሉ ችግኞችን የተተከሉ ሲሆን ቴክኖሎጂ አረንጓዴ አሻራ ካበረከታቸው በጎ ትሩፋቶች መካከል አንዱ እንደሆነና ሀገር በቀል የሆኑ ወይራ፣ ዝግባ፣ ኮሶ እንዲሁም የሀበሻ ፅድን የመሰሉ ተክሎች በአግባቡ እንዲበቅሉ የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።
የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ በአረንጓዴ አሻራ ዙሪያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገቡ እንደሆነ ገልጸው በአፍሪካ ልህቀት ማዕከል ውስጥ የታየው ቴክኖሎጂ በሌሎች አካባቢዎችም መስፋት እንዳለበት አንስተዋል።
ከችግኝ ተከላ መርኃ ግብሩ በኋላ የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰሞኑ ተወያይቶ ባስቀመጠው አቅጣጫ እንዲሁም በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ያደረገው ውይይት መቀጠሉም ተመላክቷል።
መድረኩንም የፓርቲያችን ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ እና የኢፌዲሪ ትራንስፖርት ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እየመሩ መሆናቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
ዋልታ
