ሰበር ዜና❗️
የብልጽግና መንግስት የትግራይ መከላከያ ሰራዊት (TDF) በፍጥነት ትጥቅ መፍታት አለበት በማለት ዳግም በትግራይ ላይ የጄኖሳይድ ጦርነት ለመክፈት እየሰራ መሆኑን ዛሬ አስመስክሯል፡፡ በሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በዛሬው ቀን በተደረገ ምክክር ላይ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ፍጹም ያልተጠበቀ ነው፡፡ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት የትግራይ ህገመንግስታዊ ይዞታዎች የሆኑት ራያ እና ወልቃይት ወደ ትግራይ እንዲመለሱ እየተደረገ ነው በሚል ሰዎች ተስፋ በጣሉበት በአሁኑ ወቅት እንደዚህ አይነት የጦርነት አዋጅ በትግራይ ላይ ማወጅ አስገራሚ ነው፡፡
የዛሬው የብልጽግና መንግስት መግለጫ በዋናነት መሰረት ያደረገው የትግራይ ክልል መከላከያ ሰራዊትን [Tigray Defenece Force (TDF)] ትጥቅ ለማስፈታት ያለመ ሲሆን፤ መግለጫው ዛቻ አዘል ማስጠንቀቂያ እና ማስፈራሪያ የታከለበት ነው፡፡ በመሆኑም የትግራይ ክልላዊ መንግስት ይህንን ጸረ ትግራይ መግለጫ መሰረት በማድረግ ማብራሪያ መጠየቅ እና ተገቢ ግብረመለስ መስጠት አለበት፤ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብም ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡ ደም የተጠሙ የብልጽግና ባለስልጣኖች ዳግም ትጥቅ እናስፈታልን በሚል ሽፋን ትግራይን ከቀደመው ግዜ የበለጠ እንዲያደሙ ሊፈቀድላቸው አይገባም፡፡
በቪዲዮው ላይ እንደሚሰማው የጦርነት አዋጅ መግለጫው፡-
- የህወሃት ታጣቂዎች ትጥቅ መፍታት ይገባቸዋል፡፡
- ካለፈው ስህተታቸው ሳይማሩ ዛሬም ተመሳሳይ ችግር ለመፍጠር የሚከጅሉትን ሁላችንም ተባብረን አደብ ማስገዛት ይርብናል፡፡
- ከትእግስት ቦኋላ የሚኖር ህግ ማስከበር ስራ የሚኖረውን አስከፊ ውጤት ከቅርቡ ታሪካችን ልንማር ይገባልና፡፡
- መንግስት እስከዛሬ ለትግራይ የሚያስፈልጉ የመልሶ ግንባታ እና የፋይናንስና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጉዳዮችን ሲሰራ መቆየቱ ብቻ ፍርሐት ተደርጎ ሊቆጠር አይገባም፡፡
- በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት እንደተገለጸው እና በህገመንግስቱ እንደተደነገገው እንደ ሐገር የሚኖረው አንድ የመከላከያ ሰራዊት ብቻ ነው፡፡
- ክልሎች በክልል ደረጃ ህግ ለማስከበር የሚያስፈልጋቸው ፖሊስ እና ሚሊሻ ያለፈ እንደ TDF አይነት የታጠቀ እና የተደራጀ ሰራዊት ሊኖራቸው አይችልም፤ አይገባም፡፡
- TDF ትጥቅ መፍታት እና ተያያዥ ሂደቶች (DDR) በተሐድሶ ኮምሽን እቅድ መሰረት በፍጥነት ሊተገበሩ ይገባል ብሏል፡፡
የብልጽግና መንግስት የዛሬው መግለጫ በአጭሩ TDF በፍጥነት ትጥቅ የማይፈታ ከሆነ ትጥቁን ለማስፈታት ወደ ጦርነት በመግባት ህግ የማስከበር እርምጃ እንወስዳልን የሚል ነው፡፡ ይህ መግለጫ ልክ አማራ ክልል ትጥቅ እናስፈታለን በሚል ክልሉን እንደወረረው እና እስከ ዛሬ የጦርነት አውድማ እንዳደረገው ማለት ነው፡፡ የብልጽግና መንግስት የዛሬው ድርጊት ምናልባትም የትግራይ ሐይሎች (TDF) ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ወዲህ ወታደራዊ ድጋፍ ብጠይቃቸውም፤ ለኔ ድጋፍ ከማድረግ ይልቅ ገለልተኛ ሆነዋል፤ በቀጣይ ደግሞ ከፋኖ እና ከሻብያ ጋር አብረውብኝ ለስልጣኔ አደጋ ይሆናሉ በሚል በፍራቻ ቀድሞ ለማጥቃትም ሊሆን ይችላል፡፡
እንደምናስታውሰው አቶ ጌታቸው ረዳ ከሁለት ወር በፊት በመቐለ ባደረገው ቃለመጠይቅ፤ ከ270 ሺ በላይ የትግራይ መከላከያ ሰራዊት (TDF) አለን በማለቱ ሚዲያዎች ሲቀባበሉት መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በወቅቱ የአቶ ጌታቸው ረዳ ቃለመጠይቅ አነጋጋሪ የሆነው፤ በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት መሰረት ትጥቅ ፈተዋል ተብሎ ከተዘገበው የመንግስታዊ ዜና አንጻር በመጋጨቱ ነበር፡፡ የብልጽግና መንግስት የትግራይ ሐይሎች ትጥቅ ፈተዋል በሚል ፕሮፓጋንዳ ሰርቶ የነበረው የTDF ሐይሎች ፋኖን እና ሻብያን ከትግራይ ለማስወጣት በወታደራዊ ድጋፍ የሚያግዙት መስሎት ነበር፤ ሆኖም ገለልተኛ መሆን በመምረጣቸው እና በቀጣይ ለሱ እንደተዘጋጁ በፍራቻ በማመኑ ይመስላል፡፡
በእርግጥ አቶ ጌታቸው ረዳ ከሁለት ወር በፊት ለሚዲያ ስለ TDF ቁጥርእና ቁመና መናገሩ ትክክል ነበር፡፡ ትግራይን ለመስበር የሚናፍቁ እና ወረው የሚገኙ ጠላቶች ቆም ብለው እንዲያስቡ ያደረጋቸው ዜና ነው፡፡ የብልጽግና መንግስት ሳይወድ በግድ ተወረው የተያዙ የትግራይ መሬቶችን ከሰሞኑ ከአማራ ታጣቂዎች በማስለቀቅ ቢያንስ እራሱ ለመቆጣጠር እንዲገደድ ያደረገው የትግራይ ወታደራዊ አቅም ነው፡፡ ነገር ግን የትግራይ ሉአላዊ ግዛቶች ባልተመለሱበት ሁኔታ እና በትግራዋይነታቸው ከሚሊዮን በላይ ህዝብ ተፈናቅሎ ወደ ቄየው ሳይመለስ እአተሰቃየ በሚገኝበት በአሁኑ ሰዓት፤ የትግራይ ህዝብ መብት አክስከባሪ የሆነው የTDF ሰራዊት ትጥቁን ይፍታ መባሉ ከጦርነት አዋጅ በስተቀር ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም፡፡
ይሁንና የዛሬው የብልጽግና መንግስት በተሐድሶ ኮምሽን አማካኝነት በፕሪቶሪያው አንቀጽ-6 [disarmament, demobilization and reintegration (DDR)] መሰረት TDF በፍጥነት ትጥቅ ይፍታ በሚል መግለጫ መስጠቱ ዳግም በትግራይ ላይ በትጥቅ ማስፈታት ሰበብ ጦርነት ለማወጅ የሚደረግ የጦርነት ዝግጅት መሆኑን ሁሉም የሚመለከተው አካል ማወቅ አለበት፡፡ የትግራይ ክልላዊ መንግስት እና ገዢው ህወሃት ፓርቲ የትግራይ ሉአላዊነት በአማራ ሚሊሻ እና በኤርትራ ተወሮ እና የክልሉ ሉአላዊነቱ ተደፍሮ ባለበት በአሁኑ ሰዓት፤ የብልጽግና መንግስት ይህንን መግለጫ መስጠቱ ከትግራይ ጥላቻ ስካሩ አለመላቀቁን የሚያረጋግጥ አደገኛ ነገር ነው፡፡ የዛሬውን የጦርነት መግለጫ የትግራይ ወዳጅ ሁሉ ማውገዝ አለበት ‼️
,,,
