ለትግል የመነሳት ወረፋው የእናንተ ነው
ነቃ በሉ !
በኢሀአዴግ ማህጸን ውስጥ የበቀለው አታላይ፣ ኣስመሳይ፣ ውሸታም፣ ከፋፋይ፣ ሃገርን በኤኮኖሚ ያንኮታኮተ፣ የሚልዮኖችን ህይወት በመቅጠፍ ሞትን ያለማመደ፣ በአፈና፣ በአደባባይ፣ በጎርፍ፣ በአየር፣ በጥይት፣ በእሳት፣ ቁልቁል ዘቅዝቆበመስቀል፣ በረሃብ፣ በሳንጃ እርጉዞችን በመዘልዘል የአገዳደልመንገዶችን ያስተማረ፣ በሺዎች እስር ቤት ያጎረ፣ ሚልዮኖችንያስሰደደና ያፈናቀለ፣ በዲፕሎማሲ አገርን ያዋረደ፣ ማህበራዊግንኙነታችንን የበጣጠሰ፣ የኑሮ ውድነትን ተንጠራርተንበማንደርስበት ሰማይ የሰቀለ፣ ቤቶቻችንን በላያችን ላይያፈረሰ፣ ትምህርት ቤቶችን ወደ ጦር ካምፕ ቀይሮ ሺዎችተማሪዎችን በረሃ የበተነ፣ ስራ እንፈልጋለን የሚሉ ወጣቶችንወደ ውትድርና እያፈሰ እንዲረፈረፉ ያደረገ፣ ሃይማኖታችንንያራከሰ፣ እርስ በራሳችን እያናከሰ እሴቶቻችንን የደረማመሰ፣ ሴቶችን መድፈርና ረሃብን እንደ ጦር መሳርያ የተጠቀመ፣ እያለቅን በልጽገናል የሚለን፣ ሕገ-መንግስትንና ዓለማዊህግጋትን የጣሰ፣ የራሱን ህዝብ የማስታወስ ችሎታ የሌለውጉንዳን እያለ ያራከሰ፣ የራሱን ህዝብ በውጭ አገር ወታደሮችያስጨፈጨፈ፣ የሃገሪቱን ዳር ድንበር እንዲደፈርና መሬታችንበጠላቶች እንዲወረር ይሁንታ የሰጠ፣ ሉአላዊነታችንን አደጋላይ የጣለ፣ የሃገሪቱን ፓርላማ የቤት ኣሽከሮች ያደረገ፣ ዚጎችበማንነታቸው ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ገደብ የጣለ፣ አገሪቷን በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በኮማንድ ፖስት እንድትተዳደርያደረገ አብይ አህመድ ጥቂት ሆድ አደሮችን አስከትሎአገራችን ኢትዮጵያ በዚያኛው የኢጣልያ ወረራ ዘመን እንኳንአይታው የማታውቅ ማቅ እንድትከናነብ አድርጓል።
ይህን ስንል ግን አብይ አህመድ በቅድመ ግንባር የተሰለፈሁሉንም የጥፋት ሃይሎችን ያሰባሰበ አይነተኛ እርኩስ ነውማለታችን ነው እንጂ ሁሉን የፖለቲካ ኣውታሮችን ብቻውንይዘውራቸዋል ማለታችን አይደለም። ከበስተጀርባው ከፍተኛስልጣን የያዙ አማካሪዎችና ፖሊሲ አርቃቂዎች እንዳሉ በቅጡመገንዘብ ያለብን ጉዳይ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን ግፍ አሜን ብሎ የተቀበለበት የታሪክአጋጣሚ የለም። የኦሮሞ ህዝብ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትእየተመራ የራሴን እድል በራሴ እወስናለሁ ብሎ አንገትለአንገት እየተናነቀ ነው፣ የትግራይ ህዝብ ህልውናውንሊያስከብርለት የመከላከያ ሃይል ገንብቶ በማንነቴአልደራደርም ቅጡ በማይታወቅ የብልጽግና ፓርቲምኣልደራጅም ብሎ ኣየተዋደቀ ነው። የአማራ ህዝብም የፋኖአደረጃጀቱ መስርቶ ጸረ አብይና ስርዓቱ በጦር ሜዳ መፋለምከጀመረ አንድ ዓመት አልፎታል። ወላይታ፣ ሶማሊ፣ ሃድያ፣ ሲዳማ፣ ከምባታ፣ ቅማንት፣ ኣገው፣ ጉራጌ፣ ዓፋር፣ ቤንሻንጉልጉራጌ ስንቱን ትዘረዝራለህ ሁሉም ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊማህበራዊ ወይንም ኤኮኖምያዊ ትግል ኣቀጣጥሎ አሁን ወረፋው የስርዓቱን ግበአተ መሬት የሚያበስረው የአዲስአበባና አከባቢው ሆኗል
አዲስ አበባና አከባቢዋ በብሄረሰቦች እየተካሄደ ያለውን ትግልለመቀላቀል ወረፋው ደርሷቸዋል። አዲስ አበባ ሁሉንም ብሄርብሄረሰቦች አቅፋ የያዘች መዲናችን ናት። አዲስ አበባበሃዘንም በደስታም ለብዙ ዘመናት በፍቅር አብረው የኖሩህዝቦች መኖርያም ናት። በመካከላቸው መሰረታዊ ልዩነትየለም። እነዚህ ህዝቦች ስለታፈኑ እንጂ በየክልሉ እየተደረገያለውን ግፍ ለምሳሌ የእነዶክተር አምባቸው ክነየስራባልደረቦቹ፣ የእነ አምባሳደር ስዩም መስፍንና የትግል አጋሮቹበግፍ መገደል በኦሮምያ፣ ሶማሊ፣ ቤንሻንጉል፣ ጋምቤላ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ በሁሉም ክልሎች ያለው የግፍጭፍጨፋን ጠንቅቀው ያውቁታል። በየክልሉ ከሚደረግ ግፍበባሰ መልኩ እየተጋቱት ያለ በደልም ተዘርዝሮ አያልቅም። አዲስ አበባና አከባቢዋ ሃገር ለመለወጥ በየዘርፉ ተሰማርተውሲያገለግሉ የነበሩ ጀግኖች ልጆቹ እነ እንጂነር ስመኘው በቀለ፣ ጀነራል ሰዓረ መኮነንና፣ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ በአደባባይበሴራ ሲገደሉ ወደ ውስጥ አንብቷል። አሁን ደግሞ ከአዲስአበባ በተወረወሩ ነብሰ ገዳዮች ባቴ ኡርጌሳ ተገድሎ በቆሻሻማጠራቀምያ ሲወረወር ሰምቷል። ሌሎች በሚድያ ስማቸውሊነሳ እድል ያላገኙትማ እስከ ግዜው ድረስ ወላጅ እናታቸውትቁጠራቸው።
ስለዚህ አዲስ አበባና አከባቢዋ ትግሉን ለመቀላቀል ግዜውደርሷቸዋል። የእግር ውስጥ እሳት የሆነባቸውን ጠላትጠራርገው ለመጣል የሚነሱበት ግዜ አሁን ሆኗል። የአዲስአበባ ትግል ግን ክላሽ ታጥቆ እንጦጦ ተራራ መመሸግናበሳንጃ መሞሻሎቅ አይጠይቅም። ይህ ዓይነት ትግልማየአርበኞቻችን ድርሻ ነው።አርበኞቻችን እንደ ሻማ ቀልጠንለህዝቦቻችን ብርሃን እናበራለን ብለው ስለወሰኑ ከአማራምይነሱ ከኦሮምያ ከሶማሊም ይነሱ ከቤንሻንጉል አዲስ አበባእየገቡም ሳይቀር ታሪክ መስራታቸውን እንደሚቀጥሉአሳይተውናል። ይህ ተግባር እንደሚቀጥልም ነግረውናል።
የአዲስ አበባና ኣከባቢዋ ትግል ሕገ-መንግስታዊ መብቶችንመሰረት አድረጎ የሚነሳ ፍጹም ሰላማዊ የሆነ የማያቋርጥየተቃውሞ ማእበል ነው።
አዲስ አበባ ከግብጿ ዋና ከተማ ካይሮ ከባንግላዲሽና ከኬንያበምን ታንሳለች? የካይሮ ህዝብ እ/አ/አ ጃንዋሪ 25/2011 እጅለእጅ ተያይዞ በምሬት ታህሪር ስኴር እየተባለ በሚጠራውጎዳናው ተገናኘና ግፈኛ መሪው ሆስኒ ሙባረክን በቃ! አታስፈልገንም! ስልጣንህን አስረክበንና ውረድ! የሚል መፈክርአንግቦ ሰላማዊ ሰልፍ ወጣ። ታንክና መትረየስ ሳይበግረውለተከታታይ ቀናትም ተሰለፈ። ከስልጣን ሳትወርድ ወደ ቤታችንአንመለስም የሚል ቁርጠኛ ድምጹም በሰላማዊ መንገድአሰማ። ግፈኞችና ጸረ ህዝቦች ግን በጠመንጃ ሃይል ለዘላለምስልጣን ላይ የሚቆዩ ስለሚመስላቸው ህዝብ ላይ ይተኩሳሉ። ሆስኒ ሙባረክ ያደረገውም ይህን ነበር። 846 ንጹሃንን በግፍገደለ። 6000 ንጹሃንም አቆሰለ። የካይሮ አናብስት ግን እስከአሁንም ያንኑ ያህል ገድለሃል። ስልጣን ላይ ከቆየህ ደግሞከዚህ በላይም ትገድለናለህና በዚህ ፈርተን ወደ ኋላአንመለስም። ያለ መስዋእት ድል የለም ብለው ሰልፋቸውንአጠናክሩ። ከ16 ቀናት በሁኋላ እ/አ/አ ፌብሪዋሪ 11/2011 ሆስኒሙባረክን ከስልጣን አባርረው ድል ተጎናጸፉ። ካይሮ ክንዷንአሳይታ ግፈኛውን አሽቀንጥራ ጥላለች። ብቀርቡ በባንግላድሽየተደረገውም ተመሳሳይ ነው።
አዲስ አበባ ጀግኖቿን ከጉያዋ ታቅፋ እንዴት ይህን ማድረግይሳናታል ? ገደብ ለሌለው ዘመን የግፍ ጽዋውን ለመጋትእንዴት ትፈቅዳለች? ተሰልፋ መቃወም አለባት እንጂ። የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ ብቻ ግን በቂ አይደለም። ጥበብበተሞላበት መንገድ ኤኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊትግል ማከናወንም ያሰፈልጋል።
ለምሳሌ ማንም ወጣት በዚህ የእርስ በርስ ጦርነት ገብቸ ወገንአልጨርስም እምቢ አልታጠቅም እንዲል ማስተማር፣ የአብይኣሕመድ ታጣቂዎችን በወታደራዊ መኮንኖች እየታነቀቤተስቦቹን ያለ ጧሪና የጡረታ መብት ትቶ በጦርነት እየረገፈያለው ንጹሁ ወታደር በዚህ ወገንን በሚጨርስ ጦርነት እጄንአላስገባም እንዲል ማስረዳት፣ ወደ ቤቱ እንዲሄድም መምከር፣ ተገዶ ከተዋጋም ብፍጥነት በየክልሉ የትጥቅ ትግል እያካሄዱላሉ አርበኞቻችን እጁን እንዲሰጥ መምከር፣ በከተማውናአከባቢው ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ስራ መስራት፣ የግድ ይላል።
አርበኞቻችን በተገኘ አጋጣሚ ከተማ ውስጥ እየገቡ በከፍተኛባለስልጣናት ላይ ተገቢ እርምጃ መውሰድ እንደሚቀጥሉገልጿል። እዚህ ላይ የሚኖራችሁን ሚና መገንዘብ፣ ከአማራ፣ ኦሮምያና ሊሎች ክልሎች አርበኞች ወደ ከተማው ሲገቡድርሻችሁን ማስተዋል፣ የአብይ ቀኝ ክንዶች የሚያዘወትሩበትመዝናኛና የሚኖሩበት አከባቢ ማጥናት፣ ጠላት ህዝብንለመፍጀት የሚያደርገው እንቅስቃሴና የያዘው ትጥቅ መረጃማቀበል፡ በህዝብ ላይ ግፍና መከራ የሚያደርሱ ሰላዮችናጉቦኞችን ስም ዝርዝርና መኖርያ ቦታቸውን ማጥናትናመጠቆም የመሳሰሉ የትግል መንገዶችን መጠቀም ይቻላል። እዚህ ላይ አዲስ አበቤው ልብ ማለት ያለበት አንድ ቁምነገርአለ። አብይ አህመድ የዋነኛው የሃገሪቱ የስለላ መዋቅር የኢንሳመሪ ነው። ለሆዳቸው ያደሩ ግለሰቦችን ሰብስቦ ከፍተኛየሚድያ ሰራዊት ገንብቶ በዮቲዩብ፣ ቲክቶክ፣ ፌስቡክ፣ ኢንስቶግራም ወዘተ ከፍተኛ ሃሰተኛ ወሬና ማደናገርያእንዲበትኑ አሰማርቷል። አዲስ አበቤ በዚህ መሸወድየለብህም። ይልቁንስ በፕሮፖጋንዳው ስራ በአጥፍ በልጠህመገኘት ይኖርብሃል። አራዳነትህ ለዛሬ ካልሆነ ለመች ከእንዲህ ወዲህ በአማራ፣ ትግራይ ኦሮምያ ሶማሊ ቅማንት፣ አገው፣ ሲዳማ፣ ጋምቤላና ቤንሻንጉል ጉራጌ ወዘተ ያሉአርበኞች አፈሙዛቸውና የፕሮፖጋንዳ ስራቸው የሚያቀናውወደ ጎን ወደ ወገናቸው ሳይሆን ወደ ፊት ወደ ብልጽግና ወደአራት ኪሎ ብቻ እንደሆነ ገልጿል። አስፈላጊ በሚሆንበት ግዜደግሞ እየተናበቡ በአዲስ አበባና ሌሎች ትላልቅ ከተሞችውስጥ በመግባት ይሁን በየክልላቸው የተቀናጀ እርምጃእንደሚወስዱ ይፋ አድርጓል። ሁሉም ነገር ወደ አራት ኪሎግንባር!!!
ከዛሬ ጅምሮ የህዝቦች አንድነትን የሚፈታተኑ እርምጃዎችናህዝቦችንና አርበኞቻችንን የሚያጥላላና ግጭት የሚቀሰቅስፕሮፖጋንዳ አይኖርም። አርበኞቻችንም ሕገ-መንግስትከደነገገው ክልል ውጭ ወደ ሌላ ክልል እየተንቀሳቀሱ ርስትለማስመለስ የሚደረግ ሩጫ እንዲቆም ያደርጋሉ። ሁሉምትላንትና በሕገ-መንግስት በተዋቀረው መስተዳድራቸው ብቻይንቀሳቀሳሉ። ሕገ-መንግስቱ መስተካከል አለበት ብለንብናምንም በሕግ መመራት ስላለብንና የተጣመረ እንቅስቃሴእንዲኖረን ሕገ-መንግስቱን መተሳሰሪያችን አድርገንእንንቀሳቀሳለን። ሁኔታዎች ሲመቻቹ ያለ አንዲት ጥይት ኮሽታግዝያዊ መንግስት ተዋቅሮ የአገር ሽማግሌዎችና ገለልተኛአቋም ያላቸው ከሁሉም በእኩል የተወከሉ ሙሁራንበሚሳተፉበት መድረክ በሰላማዊ ውይይት ሕገ-መንግስቱንማሻሻል ይቻላል። የሚያከራክሩ ቦታዎች ካሉም እልባትያገኛሉ። የወደፊት እጣ ፈንታችንም በነጻነት በሚደረግውይይት ይወሰናል። እዚህ ለመድረስ ግን የእድገታችን ማነቆብቻ ሳይሆን የህልውናችን አደጋ የሆነውን የአብይ ስርአትንእናንኮታኩተው።
ይህን እውን ለማድረግ ለማድረግ የሚያደናቅፉ ሁለትደንቃራዎችን በጋራ መታገል አለብን። አንደኛው ፍርሃት ሲሆንሁለተኛው ደግሞ አርስ በርስ መተማመን መጥፋቱ ነው። እነዚህ ሁለት እንቅፋቶች አብይ ኣህመድ ስልጣን ላይ እንዲቆይእየተጠቀመባቸው ያሉ ጦር መሳርያዎች ናቸውና እያንዳንዱአዲስ አበቤ ልብ ብሎ በመታገል ከትከሻው መንግሎ መጣልግድ ይለዋል። በውጭ አገሮች የተለያየ ባህል እምነትና ፍላጎትያላቸው ከተለያዩ ክፍለ አለማት የተሰባሰቡ ህዝቦችተከባብረው ሲኖሩ ኢትዮጵያዊ ግን እርስ በራሱ እንዲጫረስ፣ መተማመን ጠፍቶ አንዱ ሌላውን እየተጠራጠረውናእየጠላው እንዲኖር ተደርጓል። ይህ ተግባር የህዝብ ጠላቶችስልጣናቸውን እንዲያደላድሉ የሚጠቀሙበት ዘዴ ስለሆነሁሉም ጠንቅቆ ሊገነዘበው ያስፈልጋል። ከዛሬ ጀምሮም እርስበእርስ መጠራጠር መቆም አለበት። ፍርሃትም መከራንየሚያራዝም ስለሆነ ወገብን ግጥም ኣድርጎ መነሳትያስፈልጋል። ከሰው ልጅ ህይወትና ደህንነት በላይ አትክልቶችበሚከበሩበት ከተማ በስቃይ ከመኖር በላይ ምን ውርድትይጠበቃል?
በተጨማሪም ከሌላ ብሄረሰብ መጥተው በተለያዩ ክልሎችከሌላ ብሄረሰብ ጋር በሚኖሩ ህዝቦች ላይ ያነጣጠረ ከክልላችንውጡልን የሚል ዛቻ፣ ፉከራና ማፈናቀልና ማግለል መኖርየለበትም። በአንድ ትልቅ ብሄረሰብ ክልል ውስጥ የሚኖሩአነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሌሎች ብሄረሰቦችም ምንም ጉዳትናአድልዎ እንዳይደርስባቸውና የራሳቸውን መስተዳድርመስርተው በሰላም እንዲኖሩ አርበኞቻችን ተገቢ ከለላና ጥበቃያደርጋሉ። እንቅፋት የሚፈጥሩ ካሉ ዋናው ጠላት ላይእንዳናተኩር መሰናክሎች ስለሆኑ አርበኞቻችን የተቀናጀናየተጠናከረ እርምጃ ሊወስዱባቸው እንደሚችሉ ልብ ማለትያስፈልጋል። አንዱ ብሄረሰብ የሌላው ብሄረሰብ ወገን እንጂጠላት አይደለም።
የተለየ ፖለቲካዊ ዓላማ ያላቸው የህዝብ ተቆርቋሪ በመምሰልበአንድ ብሄረሰብ ላይ ግፍ እንዲፈጸም የሚቀሰቅሱ እንደነአብን፣ ኢዜማ፣ ኦህዴድ ብአዴን ወዘተ የመሳሰሉ የብልጽግናተላላኪዎች እንዲሁም እንደነ ሲሳይ አጌኖ ለሆዳቸው ያደሩገለልተኛ መስለው በሚድያ ህዝብን በማደናገር የግፈኛውንስርዓት ክንድ ለማጎልበት የተሰማሩ መሆናቸው በውልመገንዘብና ማጋለጥ ለዩቲዩብም እንዲዘጉ ሪፖርት ማድረግአስፈላጊ ነው።
ስለዚህ የአዲስ አበባና አከባቢው ህዝብ ጠላቶችህን ለይተህአስተውል። ጠላቶችህ አብይ አህመድ፣ የብልጽግና ማ/ኮሚቴ፣ የአብይን ስርዓት አስፈጻሚ የክልል ፕረዚዳንቶች፡ ኮሎኔልናከዚያ በላይ ያሉ የጦር መኮንኖች፣ ከየክልሉ ሸሽተው አዲስአበባ የተሰባሰቡ ጸረ-ህዝቦች፣ የመንግስት ሚኒስትሮች፣ ም/ሚንስትሮችና በሚንስትር መአርግ ደረጃ የተመደቡ፣ በጠቅላይሚንስትር ቢሮ በአማካሪነት የተሰገሰጉ፣ የደህንነት ሃላፊዎች፣ የጸጥታና የወንጀል ምርመራ ሃላፊዎች እንዲሁም እንደነሙርከኛ ሲሳይ አጌኖ የመሳሰሉ ለሆድ ያደሩ በሚድያ ስምበብሄረሰቦቻችንና በአርበኞቻችን ላይ ስም በሚያጎድፍ ተግባርየተሰማሩ፣ ህዝብን በሚያንቋሽሽ አጠራር የሚጠሩና አንዱበሌላው ላይ እንዲዘምት የሚቀሰቅሱ እንዲሁም በፓርቲ ስምየተደራጁ የቤተ-መንግስቱ ተቀላቢዎች እነ ኣብን፣ ኢዜማ፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ በእምነት ቦታዎች የተወሸቁ በሃይማኖትልባስ ህዝቦችን የሚነጣጥሉ ግለሰቦችና ከየክልሉ የህዝብንወላፈን በመስጋት ሸሽተው አዲስ አበባ የተሰብባሰቡወንጀለኞች ናቸው። የአዲስ አበባና አከባቢው ጣቶች በነዚህላይ ብቻ ይቀሰራሉ። የተቀረው ህዝብ በሃይማኖት፣ በብሄር፣ በጾታ፣ በእድሜና በሌላ ሳይከፋፈል ኣብሮ ይሰለፋል።
ይህ ሰልፍ አብይ ስልጣኑ እስኪለቅ ድረስ ሁሉም የአዲስ አበባናአከባቢው ህዝብ አንድ ላይ የሚወጣበትና ለተከታታይ ቀናትየሚከናወን መሬት አንቀጥቅጥ ማእበላዊ ሰልፍ ነው። የሚጀመርበት ቀንና ቦታ በቅርብ ግዜ ይገለጻል። እስከዚያውበቂ ዝግጅት ይደረግ። በዚህ ወቅት የሚስተጋባው መፈክርአብይ አህመድ በቃህ! ስልጣንህን አስረክበህ ከቤተ መንግስትውጣ! በቃን! ከዚህ በላይ በደል መሸከም አንችልምና ውረድ! የሚል ይሆናል።
ይህ ግፈኛው መንግስት የድጋፍ ካልሆነ የተቃውሞ ሰልፍአይፈቅድም። ያልፈቀደው ሰልፍ ሲካሄድ ደግሞ ሰውን ያስራልያሰቃያል ይገድላል። ስለዚህ ይህን ሰልፍ የሚያስተባብሩቢኖሩም ለደህንነታቸው ሲባል በግልጽ ስማቸው እየተገለጸአይቀርቡም። ይልቁንስ በህዝባቸው ውስጥ ሆነውየሚቀሳቀሱ ናቸው። ሁሉም የአዲስ ኣበባና አከባቢውህዝብም የሰልፉ አስተባባሪ ይሆናል። በየተራ እየተደማመጠበጨዋነትና በወኔ መፈክር ያሰማል። በዚህ ሰልፍ ምንምአይነት ድንጋይ፣ ብትር፣ ስለት፣ ጦር መሳርያ ይዞ መግባትበጥብቅ የተከለከለ ነው። ማንም ሰልፈኛ ታጣቂዎች በህዝብላይ ለመተኮስ እድል የሚያገኙበትን አንዲት በር መክፈትየለበትም። ድንጋይ ውርወራ በፍጹም አይፈቀድም። ለተናካሽውሻ በእግርህ ለመከላከል መሞከር እንካ ስጋ ማለት ነውእንደሚባለው በለበስከው ልብስ ላይ አረንጓዴ ብጫ ቀይ ቀለምአለ ብሎ በሚገድል መንግስት ፊት በህገ መንግስቱ ያልጸደቀበልማድ ልሙጥ እየተባለ የሚጠራውን ባንዴራ ይዘህ መሰለፍለአደጋ የሚያጋልጥ ስለሆነ በፍጹም አይፈቀድም።
ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች እንዲገድል፣ እንዲያስርና እንዲዘርፍ እየተደረገ ስለመጣበመካከላችሁ ውስጥ ጥላቻ እንዲስፋፋና አንዱ ሌላውንእንዲጠራጠረው ተደርጓል።.
ቅልብ ሚዲያዎቹና ለሆዳቸው ያደሩ ተከፋዮችም የተለያዩአጀንዳዎችን እያነሱ በተለያዩ ሚዲያዎች በስፋት የማደናገርስራቸውን እያጧጧፉ
ነው። ጸረ ህዝቦች የስልጣን እድሜአቸውን የሚያራዝሙትየግለሰቦችና የብሄሮችን ስም እያነሱ በማጠልሸት፣ በመካከላችን መተማመን
እንዳይኖር በማድረግና በጎሪጥ እንድንተያይ በማድረግነው። በዚህ የተለመደው ተግባራቸው እርስ በእርሳችንእንድንናከስ ይፍጨረጨራሉ።
አሁን ይህን ሰብራችሁ በመውጣት፣ በመካከላችሁ ፍቅርናመተሳሰብን ማጎልበትና አንድነታችሁን እንደ ብረት ማጠንከርየወቅቱ አብይ ጉዳያችሁ
ሆኗል። ስለሆነም ዛሬ በምንም ምክንያሳት ሳትለያዩ እጅለእጅ ተያይዛችሁ ታሪክ የምትሰሩበትና ለነገ መሪዎቻችሁምትምህር የምታስተላሉፉበት
ሰልፍ ማካሄድ የዘመኑ ጥያቄ ሆኗል። ጀግና በወሬአይፈታም። እነሱ ሲጮሁ እናንተ ስራችሁን ስሩ።
2- የአብይ መንግስት በሴራ የተተበተበ ስለሆነ በሰልፈኛውመሃል ሁከት የሚቀሰቅሱ ጥይት የሚተኩሱ ሰላዮችንሊያሰማራ ይችላል። እነዚህን
እየተከታተልን ኣደብ ማስገዛት አስፈላጊ ነው።
3 – አብይ ጸረ ዴሞክራሲ ነውና ሰልፉ እንዳይካሄድ አስቸኳይግዜ አዋጅ ሊያውጅ ይችላል። ማስፈራራቱም እስራቱምይቀጥላል። የአዲስ አበቤና
አከባቢው ህዝብ ምርጫ ሁለት ነው። ይህን ተቋቁመህነጻነትህንና መብትህን ማስከበር አልያም አብይ እናቱየተነበዩለት የሚለንን ንግስና
እስኪጨርስ የመጣውን ግፍ እየተቀበልክ መቀጠል ነው። ስለሆነም አዲስ አበቤና የአከባቢው ህዝብ ማለቅያ ለሌለውግፍ ራሱን ማዘጋጀት
እንደማይፈቅድ በተግባር ማሳየት አማራጭ የሌለው የዛሬምርጫው ሆኗል።
4-የፖለቲካ ፓርቲዎች በራሳችሁ ውስጣዊ ድክመትና በአብይመንግስት አውዳሚ ተግባር ህልውናችሁ የተመናመነእንደሆነና አንዳንዶቻቹሁም
ለሆድ ማደራችሁን ተገንዝበናል። እናንተ ለህዝባችንእንቆረቆራለን የምትሉ ቆራጥ ታጋዮች በእነዚህ ወሳኝ ቀናትከህዝባችሁ ጎን እንድትሰለፉ
በክብር ተጋብዛቹኋል።የጦር መሳርያችን አፈሙዞችና የፕሮፖጋንዳ ብእሮች በሙሉወደ አራት ኪሎ ያነጣጥሩ!!!
ጥብቅ መልእከት ለመከላከያ፣ ፖሊስ፣ ምልሻ፣ ሌሎችታጣቂዎችና የደህንነት አባላት
ዘለኣለማዊ የሚባል መንግስት የለም። ህዝብ ግን ኗሪና ዘለቂነው። የእናንተ ሃላፊነትም ለሕገ-መንግስቱና ለህዝብ ተገዢመሆን ነው። እናንተም የህዝቡ አካል እንጂ ጠላቶችአይደላችሁም። ስርዓቱ በአንድ ሰው ወደሚመራ አረመኔና ጸረህዝብነት ስለተቀየረ ይህን ኣስክከፊ ስርዓትን አናገለግልምእያላችሁ ጥላችሁት ውጡ። ህዝብ ብሶቱን ለመግለጽ ሲወጣከጎኑ ተሰለፉ። ሰልፈኛው ሕገ መንግስታዊ መብቱን በሰላማዊመንገድ ለማስከበር ሲነሳ ምንም ጉዳት እንዳይደርስበትምከለላ እንድትሰጡና ካይሮ የታየውን ህዝባዊ ወገንተኝነትእንድታስመሰክሩ ማስገንዘብ እንፈልጋለን። ጨልሞአይቀርምና ይነጋል። ነገ በታሪክ እንዳትወቀሱና በግፈኛነትከመጠየቅ እንድትርቁም ወገንናዊ ጥሪያችንን እናደርሳለን።
በተለይ የኦሮሞ ተወላጅ ለሆናችሁ የመንግስት ደጋፊዎች
ይህ መንግስት የኦሮሞ መንግስት እንዳይደለና የኦሮሞ ህዝብእየደረሰበት ያለውን ግፍ ከማንም በላይ እናንተውጠንቅቃችሁ ታውቁታላችሁ። ይሁን እንጂ አንዳንድ ጉርሻተከፋዮች የአብይ አህመድ መንግስት የኦሮምያ መንግስት ነውእያላችሁ ህዝብን በማደናገር የተሰማራችሁ እንዳላችሁተገንዝበናል። የአብይ መንግስት በኦሮሞ ትከሻና ህይወት ወደስልጣን መጥቶ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ግፍ እያስተናገደእንደሆነ በክልሉ ውስጥ ያሉ 30 እስር ቤቶች፣ በእነዚህ እስርቤቶች ያሉ ከመቶ ሺ በላይ እስረኞች፣ ቤተሰቦችና ጉዳተኞች እነመሓመድ አሚን፣ ገላና ኢማና፣ ኩሊ ሃዋስ፣ ኣማኑኤልወንድሙ፣ አርቲ ኑነንዲና መንደራቸው የተቃጠለባቸው፣ ከብቶቻቸው የተዘረፉባቸውና ቤተሰቦቻቸው ያለቁባቸውህያው ምስክሮች ናቸው።ለገጣፎ፣ ቡራዩ፣ ሰበታና ሸገር አብይአህመድ ተነካ ብሎ ይንነሳል ብሎ መገመት የሚያመለክተውየህዝቡን ስቃይ አለመረዳትና ለመደባብበቅ መሞከር ነው.።
ስለሆነ ከአብይ ጋር ተሰልፋችሁ የኦሮሞን ህዝብ ስቃይከማራዘም ተቆጠቡና ከወገኖቻችሁ ጎን ተሰለፉ። አለበለዝያከፍተኛ ግፍ እየደረሰባቸው ባሉ የኦሮሞ ልጆች መቀለድ ማለትስለሆነ የነገ ተጠያቂነታችሁ የከፋ እንደሚሆን ከወዲሁእንመክራለን። ከሌሎች ብሄረሰቦች የሚነጥላችሁ፣ ህሊናችሁየሚወቅሳችሁና የሚያስጠይቃችሁ ተግባር ከመስራትተቆጥባችሁ ከሌሎች ብሄረሰቦች ወገኖቻችሁ ጎንእንድትሰለፉ ወገናዊ ምክራችንን እንለግሳለን።
አዲስ አበባና አከባቢው
ለትግል የመነሳት ወረፋው የናንተ ነው።
ነቃ በሉ !
ለሚድያ ሰዎች
ይህን መግለጫ ስታቀርቡ ከሚክክከተሉት የብሄረሰቦችሙዚቃዎች መርጣችሁ ኣንደ ባክግራውንድ መጠቀምትችላላችሁ
ኦሮሞ — https://youtu.be/DHG9jkqs6UE
ትግራይ — https://youtu.be/hEJRyX7-DQQ
ሙርከኞች – https://youtu.be/NTVf1fo2HS4
ቅማንት – https://youtu.be/pzkzEE-NDFQ?si=2RSofeRlSr2Bg-Xf
ሶማሊ – https://youtu.be/duMFknf1eyg?si=TN5D2p2PpzzoxqcB
አገው – https://youtu.be/ovqaPMiBwrE?si=10FPfx256BAcIivU
ወላይታ – https://youtu.be/hjXwKpxLp-U?si=er6DJtwRH-urjAcA
ጉራጌ – https://youtu.be/RzNxxgdrhZY?si=lJtTspI32K_INJjg
አማራ — https://youtu.be/ptZyeGanLWk
የብሄሮች ኣጋርነት
Solidarity of Nations
1 – አዲስ አበቤና የአከባቢው ህዝብ አንድ ላይ እንዳይሰለፍየአብይ ስርዓትና ለሆዳቸው ያደሩ ተላላኪዎች ባቀነባበሩት ሴራአንዱ ሌላውን
