የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጻህፍት አገልግሎት በመተባበር በሸገር ከተማ ለሚገኙ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት መርጃ የመማሪያ እና የማስተማሪያ መጻህፍት ድጋፍ አደረጉ ፡፡
በቀጣይ በሌሎች ክልሎች ተመሳሳይ ስራዎችን በመስራት ዜጎች የንባብ ባህላቸውን እንዲያሳድጉ በማድረግ ትውልድ የማነጽና የመገንባት ስራ የሚሰራ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ ገልፀዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከዚህ ቀደም በቤንሻንጉል ፣በደቡብና በአማራ ክልሎች የመጻህፍት የድጋፍ ማድረጉ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ምንጭ፡ ኢዜኣ
