Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

“የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ በማቋቋም ሂደት ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ግንዛቤ በመፍጠር ገንቢ ሚና ሊጫወቱ ይገባል” -አምባሳደር ተሾመ ቶጋ



የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት እና መልሶ በማቋቋም ለአገር ሰላምና ግንባታ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ በሚደረገው ጥረት መገናኛ ብዙሃን ግንዛቤ በመፍጠር ገንቢ ሚናቸውን እንዲወጡ የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ጥሪ አቀረቡ።

የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ ማደራጀትና መልሶ በማቋቋም ሂደት የመገናኛ ብዙኃን ሚናን የተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ነው።

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ እንዳሉ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት ተኩስ ለማቆም የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት ቅድሚያ የተሰጠው ጉዳይ እንደነበር አስታውሰዋል።

የቀድሞ ተዋጊዎች የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ትጥቃቸውን ፈተው መደበኛ ሕይወታቸውን በመምራት ለአገር ሰላም ልማትና ዴሞክራሲ አበርክቶ እንዲኖራቸው ለማስቻል ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም ከኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ስምምነት በኋላ የነበረውን የመልሶ ማቋቋም እና የሌሎች አገሮችን ጭምር ልምድ መወሰዱን አመልክተዋል።

መልሶ ለማቋቋም የፋይናንስ ሎጂስቲክስ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ወሳኝ መሆናቸውን ነው አምባሳደሩ ያስገነዘቡት። ምርታማና ሰላማዊ ሕይወት መምራት የጀመሩ የቀድሞ ተዋጊዎችን ማፍራት የተቋሙ ተልዕኮ ነው ብለዋል።

ከዚህም አኳያ በሰባት ክልሎች ያሉ ከ371 ሺህ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት መልሶ ማቋቋም ሂደት ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ለተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎችና ሲቪክ ድርጅቶች በማስተማር ገንቢ ሚና ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ሐምሌ 12 ቀን 2015 ዓ.ም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *