የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ ከ12 ዓመታት ቆይታ በኋላ የአረብ ሊግ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ሳውዲ አረቢያ መግባታቸው ተገለጸ።
ከግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በላይ ከቀጠፈው ጦርነት በኋላ ሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳውዲ አረቢያ በምታስተናግደው የአረብ ሊግ የመሪዎች ጉባኤ ላይ እንደምትሳተፍ ተገልጿል።
ሶሪያ ከዚህ ቀደም ተቀዋሚ ኃይሎችን ሲደግፉ የነበሩ የአረብ ሀገሮች የአላሳድን በስልጣን የመቆየት ጉዳይ በመቀበላቸው ምክንያት ወደ ሊጉ ለመመለስ በቅርብ ወራት መወሰኗን ዘገባው ጠቅሷል።
በቅርቡ በቱርክ እና ሶሪያ በተከሰተው ርዕደ መሬት ባላንጣ የነበሩ አካላት የነፍስ አድን እርዳታ ለማቅረብ በጋራ መረባረባቸው አንዱ መነሻ እንደሆነ ተጠቅሷል።
ፕሬዝዳንት አሳድ በጉባኤው ለመሳተፍ ጅዳ የገቡ ሲሆን የአዘጋጅ ሀገር የሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጨምሮ ሌሎች አባል ሀገራት በሶሪያ እንደገና መመለስ ደስታቸውን ገልጸዋል።
ከአባል ሀገራቱ ኳታር የአሳድን መመለስ እንደማትደግፍ እና ከሊጉ ሀገራት ስምምነት ውጭ እንደሆነ ገልፃለች።
ሶሪያ አሁንም ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ እንዳለባት የጠቆመው የቢቢስ ዘገባ፣ ከ15 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል።
ኢቢሲ
