የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች የሰባት ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡
የሱዳን ተፋላሚ ሃይሎቹ በአሜሪካ እና ሳዑዲ ዓረቢያ አደራዳሪነት በሳዑዲ ሲያካሂዱት የቆዩት ውይይት ተጠናቋል፡፡
ውይይቱን አስመልክቶ ዋሽንግተን እና ሪያድ ባወጡት የጋራ መግለጫ እንዳስታወቁት÷የሱዳን ጦርና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች የ7 ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
የተኩስ አቁም ስምምነቱም ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ነው የተገለጸው፡፡
ከዚህ በፊት በተፋላሚ ሃይሎቹ መካከል የተደረሱ የተኩስ አቁም ስምምነቶች ተግባራዊ አለመደረጋቸው ተመላክቷል፡፡
አሁን ላይ የተደረሰው ስምምነት በትክክል ተግባራዊ እንዲደረግም ሒደቱን የሚቆጣጠር አካል እንደሚዋቀር ተጠቁሟል፡፡
ፋና
