የሰላም ሠራዊት አባላቱ የከተማዋን ሰላም እና ፀጥታ ዘላቂ እና አስተማማኝ እንዲሆን በማስቻል በኩል የማይተካ ሚና መጫወታቸውን የአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።
የአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸሙን በተመለከተ በከተማዋ ከሚገኙ ከ1 ሺህ በላይ የሰላም ሠራዊት አባላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።
ባለፉት 9 ወራት ከ2 ሺህ በላይ የወንጀል ድርጊቶችን በማጋለጥ እና ተጠርጣሪዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ በማድረግ ረገድም የሰላም ሠራዊት አባላቱ የላቀ ሚና እንደነበራቸው በመድረኩ ተገልጿል።
በተጠቀሰው ወቅት ከ1 ሺህ 500 በላይ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ስር መዋሉም ተገልጿል ሲል አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘግቧል።
ኢዜኣ
