Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
ዜና ትግርኛ
0

የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎችና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የጋራ ውይይት አካሄዱ

የሰላም ሚኒስቴር ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፍትህና የህግ ጉዳዮች ቢሮ ጋር በመተባበር የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎችና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የጋራ የውይይት መድረክ ማካሄዱን አስታውቋል።

በመድረኩ ላይ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፍትህና የህግ ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አብደላ በከር እንደገለጹት ስለ ሰላም የምንሰራው ግጭትና ብጥብጥ ውስጥ ከገባን በኋላ መሆን እንደሌለበትና ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የአጎራባች ክልሎች የእርስ በእርስ ግንኙነትና መናበብ በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡

የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና ግጭት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ስዩም መስፍን (ዶ/ር) በበኩላቸው የመንግስታት የጎንዮሽ፣ ክልል ከክልል ያለው ግንኙነት በትብብርና ህግን መሠረት ባደረገ መልኩ መሆን አለበት ብለዋል፡፡

የፌዴራሊዝም ስርዓት ያለ መንግስታት ግንኙነት ጠንካራ ሊሆን እንደማይችል የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው በክልሎች መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶች ክልሎች ራሳቸው በሰከነ መንገድ የመፍታት ባህልን ሊያዳብሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ከሰላም ሚኒስቴር፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በመጡ ኃላፊዎችና ምሁራን ጥናቶች ቀርበው ውይይት እንደተደረገባቸው ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ዋልታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *