ባለፉት ሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው 2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የመጀመሪያው ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ብሔራዊ ፈተና መጠናቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡ አገልግሎቱ በሂደቱ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡
የሁለተኛው ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ይሰጣል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢና ሳውላ ካምፖስ ተገኝተው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ሂደትን ተመልክተዋል፡፡
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተማሪዎች ፈተናቸውን በተረጋጋ ሁኔታ መውሰዳቸውን ጠቅሰው፣ ተፈታኞች ፈተናውን በተቀመጠው ደንብና መመሪያ እንዲሁም በመልካም ስነምግባር በማጠናቀቃቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ቅዳሜና እሁድ ወደ መፈተኛ ማዕከል በመግባት የፊታችን ሰኞ ደግሞ ገለጻ እንደሚሰጣቸውና ፈተናውን ተጠቁሟል፡፡ ከማክሰኞ ጀምሮ እስከ አርብ ድረስ እንደሚወስዱ ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢፕድ
