የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የመዝናኛውን ኢንዱስትሪ የስራ እድል ፈጠራ መስክ ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረገ።
በመድረኩ የባህልና የጥበብ ፈጠራ ኢንዱስትሪ የሥራ ዕድል ማስፋፊያ እና ግብይት ልማት ዘርፍ ላይ የመነሻ ሀሳብ በማቅረብ ከባለድርሻ አከላት ጋር ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የስራ እድል ማስፋፊያ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዘሪሁን አለማየሁ ሚኒስቴሩ ለ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው በጥበብ ዘርፉ ሰፊ የስራ እድል ለመፍጠር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የጥበብ ስራዎች የሚስተዋሉ ማነቆዎችን በመፍታት ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር የሚያስችል ቅንጅታዊ የአሰራር ሥርዓትን መዘርጋት እንደሚያስፈልም ተገልጿል።
