የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት 15ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ነው።
በጉባኤው ላይ የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
የሀይማኖት ተቋሙ የሰላም እና እሴት ግንባታ ላይ ለመስራት የድርሻውን እየተወጣ ነው ተብሏል።
በሀገሪቷ ህዝቦች እና የእምነት ተቋማት ላይ ያለውን ለዘመናት የቆየ የመከባበር ባህል በማጠናከር ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ ሀይማኖታዊ እሴትን መሰረት አድርጎ እየሰራ መሆኑም ነው የተገለጸው።
ሀገራዊ የሰላም እና የመከባበር እሴት ግንባታ ላይ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ በጉባኤው የተገለጸ ሲሆን አሁንም ቀሪ ስራዎች መሰራት እንደሚጠበቅባቸው ተመላክቷል።
ጉባኤው የ2015 እና የ2016 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ውይይት ያደርጋል።
