Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ዛሬ ጉንበት7/2016ዓ/ም በብልፅግና እና በህወሓት መካከል የተደረገው ሦስተኛው ዙር የሁለትዮሽ የፖለቲካ ውይይት ተካሄዷል

ዛሬ ጉንበት7/2016ዓ/ም በብልፅግና እና በህወሓት መካከል የተደረገው ሦስተኛው ዙር የሁለትዮሽ የፖለቲካ ውይይት ተካሄዷል::

በድርድሩ ቀደም ብሎ የተደረሰውን የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነት መርሆዎችን በማስታወስ በዋና ዋና አጀንዳዎች ቅደም ተከተል ላይ ከተወያዩ በኋላ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ሁለቱ ወገኖች ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል። በመጨረሻ

  1. በቅርቡ በራያ በተፈጠረው ግጭት ላይ ዝርዝር ውይይት ማድረግ; ክስተቱ መከሰት ያልነበረበት እና ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ሂደቱን የሚጻረር ነው ሲሉም ተስማምተዋል።
  2. ሁለቱም ወገኖች የየራሳቸውን የፖለቲካ ሚና በመጫወት ማንኛውንም ችግር በሰላማዊ መንገድና በውይይት ለመፍታት በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተዋል። በዚህ ረገድ የሰላም ሂደቱን የሚያጠናክር እና በግንኙነት ተግባራቸው ላይ ግጭትን ከሚፈጥር ይዘት እንዲታቀቡ ተስማምተዋል።
  3. የግጭት ምልክቶችን በጋራ ለመከላከል እና በፍጥነት ለመቆጣጠር በትኩረት ለመስራት ተስማምተዋል።
  4. ሁለቱም ወገኖች የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተግባራዊነትን ለማመቻቸት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ተስማምተዋል.

በሌሎች አጀንዳዎች ላይም ውይይት እንዲቀጥል በመስማማት ውይይቱን አጠናቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *