የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ የፌደራሉ መንግሥት እና ህወሓት በሰሜን ኢትዮጵያ ሲካሄድ የቆየውን የእርስ በርስ ጦርነት ለማስቆም ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም. የሰላም ስምምነት ከፈረሙ በኋላ የአማራ ኃይሎች ከአካባቢው አስተዳደር ጋር በተመተባበር የትግራይ ተወላጆች በኃይል ከምዕራብ ትግራይ እንዲለቁ እያደረጉ ነው ብሏል።
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጥቅምት 2013 ዓ.ም. ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የአማራ ኃይሎች እና በአካባቢው የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር በትግራይ ተወላጆች ላይ የጦር ወንጀል እና በሰብዓዊነት ላይ ወንጀል በመፈጸም የዘር ማጽዳት ፈጽመዋል ብሏል ቡድኑ።
የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ተቋም በቅርቡ ባካሄደው ጥናት ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ድርጊት ተጠያቂ የተደረጉት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እና በላይ አያሌው የተባሉ ግለሰቦች አሁንም ከሕግ ውጭ በማሰር፣ በማሰቃየት እና የትግራይ ተወላጆችን በኃይል በማፈናቀል ተግባር መሰማራታቸውን አመልክቷል።
በይገባኛል ከሚወዛገቡባቸው ቦታዎች መካከል አንዱ ሲሆን፣ በ2013 ዓ.ም. የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በአማራ ክልል ኃይሎች ቁጥጥር ስር ገብቶ ወልቃይት ጠገዴ በሚል በክልሉ ስር ይገኛል።
ለሁለት ዓመታት የተካሄደውን የእርስ በርስ ጦርነትን ያስቆመው የፕሪቶሪያው ስምምነትን ተከትሎ የተቋቋመው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፌደራሉ መንግሥት የአማራ ኃይሎችን ከምዕራብ ትግራይ እና ከሌሎችም የክልሉ አካባቢዎች እንዲያስወጣ እየጠየቀ ነው።
ለረጅም ጊዜ የቆየ የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸውን ምዕራብ ትግራይን ጨምሮ ሌሎችንም አካባቢዎች የሚያስተዳድረው የአማራ ክልል መስተዳደርም ጥያቄው ሕጋዊ መፍትሔ እንዲሰጠው ሲጠይቅ ቆይቷል።
የፌደራል መንግሥቱም የወሰን ይገባኛል ጥያቄዎች በሕገ መንግሥቱ መሠረት ምላሽ እንደሚያገኙ እንደሚደረግ በተለያዩ ጊዜያት ገልጿል።
