Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
Economyአማርኛ ዜና
0

ከ8 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ኩባንያዎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ


ከ8 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ አስር የሀገር ውስጥ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው መሥራት የሚያሰችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።

የስምምነት ፊርማውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ ከአስሩ ኩባንያዎች ተወካዮች ጋር ተፈራርመዋል።

ኮርፖሬሽኑ በሀገሪቱ የአምራች ዘርፉን ለማጠናከር በርካታ ሥራዎች እየሠራ እንደሚገኝ አቶ አክሊሉ ታደሰ በዚሁ ወቅት ገልጸዋል።

በተለይም የግል ባለሀብቶች ተሳትፎ እንዲጨምር ማድረግ እና የአገር ውስጥ ኩባንያዎችን ማበረታታት ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት በኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው መሥራት የሚያሰችላቸውን ስምምነት የተፈራረሙ ኩባንያዎች ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድም ትልቅ አስተዋጥኦ ይኖራቸዋል ብለዋል።

ከአስሩ ኩባንያዎች ውስጥ አምስቱ በመድኃኒት ማምረት ዘርፍ የሚሰማሩ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ይህም ኢትዮጵያ የሕክምናውን አገልግሎት ለማሳለጥ የምታወጣውን የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረት የሚደረገውን እንቅስቃሴ እንደሚያግዝ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *