Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ከቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች የተሰጠ መግለጫ


  1. የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ በተመለከተ
    በጦርነቱ ምክንያት ከምዕራብ ትግራይ እና ደቡብ ትግራይ፣ ከኢሮብ ወረዳ፣ ሰሜን ምዕራብ ትግራይ እንዲሁም የኤርትራ አዋሳኝ አከባቢዎች በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከመኖርያ ቀዬአቸው የተፈናቀሉ መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም እስከ አሁን ድረስ ወደ ቀያቸው ሳይመለሱ በከባድ ችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የፕሪቶርያውና የናይሮቢ የሰላም ስምምነት ከተደረገ ከስድስት ወራት በላይ ያቆጠረ ቢሆንም በስምምነቱ መሰረት ተፈናቃዮቹ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እየተደረገ ባለ መሆኑ የሚያሳስብ ነው፡፡ ስለሆነም ተፈናቃዮቹ ከክረምት በፊት ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ ካልተደረገ ከፍተኛ የሆነ የሰብአዊ ቀውስ ይገጥማቸዋል፡፡
    በተጨማሪም በሱዳን በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙት የምዕራብ ትግራይ ተፈናቃዮች በአደጋ ውስጥ ይገኛሉ፡፡
    ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግስት፣የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲሁም ጉዳዩን የሚከታተሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና መንግስታት በተፈናቃዮቹ ላይ እየደረሰ ያለው ከፍተኛ የመብት ጥሰት ግምት ውስጥ በማስገባት ተፈናቃዮቹ ከክረምት በፊት ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ድርጅታችን ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ያሳስባል፡፡
  2. በማንነታቻው ምክንያት በእስር ላይ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች በተመለከተ
    በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች እና በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች በማንነታቸው ብቻ ታስረው የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እንጠይቃለን፡፡ በተለይ ደግሞ በጎንደር፣ ደባርቅ፣ ደሴ፣ ሽዋሮቢት፣ ወልድያ እና ሌሎች ከተሞች ታስረው የሚገኙ ስለመሆናቸው ባደረግነው ማጣራት ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ እነዚህ የትግራይ ተወላጆች በአብዛኛው ክሳቸው ከህወሀት ጋር በመተባበር የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ሲሆን ህወሓት ከሽብርተኝነት ከተሰረዘች በኃላም ለወራት በእስር ላይ እየማቀቁ መቀጠላቸው ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥሰት በመሆኑ ከእስር እንዲለቀቁ እንጠይቃለን፡፡
    Human Rights First

ግንቦት 09 ቀን 2015

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *