Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

‹‹ኢትዮጵያ ዋነኛ የጀርመን የልማት አጋር ነች›› በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውር


ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት ዋነኛዋ የጀርመን አጋር ናት ሲሉ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውር ተናገሩ፡፡

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውር ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ጀርመን በተለያዩ ዘርፎች አጋርነት ከፈጠረችባቸው 12 የአፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ዋነኛዋ ናት።

ኢትዮጵያና ጀርመን በሁለትዮሽ ብቻ ሳይሆን በባለብዙ ወገን ግንኙነትም ላይ በንቃት ተሳትፏቸውን እያሳደጉ ይገኛል። እንደ አምባሳደር ስቴፈን ገለጻ፤ ኢትዮጵያና ጀርመን በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በመልካም አስተዳደር ማስፈን፣ እንዲሁም በአሳታፊና ሰላማዊ ማኅበረሰብ ላይም ግንኙነታቸውን አሳድገዋል።

በዘላቂ የልማት ዘርፎች፣ በኢኮኖሚ፣ በሥነ-ምሕዳርና በማኅበረሰብ ልማት ውስጥ የሚያደርጉትን ትብብር እያጠናከሩ ይገኛል ሲሉ አመላክተዋል።

ግንኙነታቸው መንግሥት ለመንግሥት ብቻ ሳይሆን የግሉን ሴክተርም ያካተተ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *