Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ኢትዮጵያ እና ጀርመን የ25 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ እና ጀርመን የ25 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ።

የድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና በጀርመን ልማት ባንክ የአፍሪካ ህብረት እና የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ክርስቶፍ ቲስኬንስ ተፈራርመውታል።

ድጋፉ በገጠራማው የሀገሪቱ ክፍል ያለውን የግብርና ሰንሰለት ለማጠናከር የሚተገበረውን ፕሮጀክት ለማሻሻል የሚያግዝ ነው ተብሏል።

ይህም በምስራቅ ጎጃም እና አርሲ ዞኖች የሚተገበር መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

የዚህ ፕሮጀክት ዋና አላማ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ እና ዘላቂነት ያለው ሥነ ምህዳር ለመተግበር፥ የግብርና ምርታማነትን መጨመር እና ከፍተኛ የዝናብ መጠን በሚያገኙ አካባቢዎች የገበያ ተደራሽነትን ማስፋት መሆኑ ተጠቅሷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *