Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ የ106 ሚሊዮን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ


ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) የ106 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በተካሄደ ሥነ ሥርዓት ተፈራረሙ።

ገንዘቡ ከIFAD (78.2 ሚሊዮን ዶላር)፣ ከአውሮፓ ኅብረት (17.84 ሚሊዮን ዶላር) እና ከASAP Grant (10.5 ሚሊዮን ዶላር) የተሰባሰበ መሆኑ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።

ከድጋፉ የሚገኘው ገቢ በኢትዮጵያ የአሳታፊ ግብርና እና የአየር ንብረት ለውጥ (PACT) ፕሮግራም ትግበራ ይውላል።

የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ በተመረጡ የገጠር ቀበሌዎች የ150 ሺህ ቤተሰቦች ገቢን፣ ምግብን እና አመጋገብን በዘላቂነት ማሻሻል እና የአየር ንብረት ለውጦችን የመቋቋም አቅምን መገንባትም እንደሆነ ተገልጿል።

ፕሮግራሙ ሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞች ላይ የሚያተኩር ሲሆን ድህነትን ለመቀነስ እና የመቋቋም አቅምን ለማሻሻል የተነደፈ ነውም ተብሏል።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ እና የዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ የምሥራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ክልል ዳይሬክተር ሣራ ምባንጎ-ቡን ተፈራርመዋል።

ምንጭ፡ ኢዜኣ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *