በፌዴሬሽን ም/ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ዛህራ ሁመድ የተመራ ልዑክ በስዋዚላንድ ማንዚኒ ከተማ የአፍሪካና የዓረቡ ዓለም ም/ቤቶች ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው።
በጉባዔው ላይ የተለያዩ የአፍሪካና የዓረቡ ዓለም አፈ ጉባዔዎች፣ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶችና ሌሎች ልዑካን ቡድኖች እየተሳተፉ መሆኑን የፌዴሬሽን ም/ቤት መረጃ ያመላታክል፡፡
በዓለም እያጋጠሙ ያሉ የተለያዩ ቀውሶች በአፍሪካና በዓረቡ ዓለም ኢኮኖሚ ላይ በሚያሳርፉትተፅዕኖ ላይ ጉባዔው የሚወያይ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
ከዚህም ባለፈም የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ለዘላቂ ልማት ያለው አስተዋፅኦ ላይ በስፋት እንደሚመክር እና ወ/ሮ ዛህራም ኢትዮጵያን ወክለውንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ፋና
