ኢትዮጵያና ጣሊያን የ7 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ የድጋፍ ሥምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የድጋፍ ሥምምነቱን በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ እና በኢትዮጵያ የተመድ ፕሮጀክቶች ማስተባበሪያ ቢሮ ዳይሬክተር ወርቅነሽ መኮንን ተፈራርመውታል፡፡
ድጋፉ በአፋር እና ደቡብ ክልሎች በጤና፣ ትምህርትና የንጹሕ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ የሚሠሩ የመልሶ ግንባታሥራዎችን እና መሠረተ ልማቶችን ለማሻሻል እንደሚውል የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡
አምባሳደር አጎስቲኖ ÷የጣሊያን መንግስት በኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭትሳቢያ እና በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ጉዳት የደረሰባቸውን የማኅበረሰብ ክፍሎች መደገፍ በመቻሉ መደሰቱን ተናግረዋል፡፡
Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
