Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ኢራን እና አሜሪካ ኦማን ውስጥ በሚስጥር እየተደራደሩ መሆናቸው ተሰማ

ኢራን እና አሜሪካ በኦማን ዋና ከተማ መስከት በሚስጥር ድርድር እያደረጉ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

በዚህ ድርድር ሁለቱ አገሮች በጊዚያዊነት ስምምነት ላይ በመድረስ አሜሪካ በኢራን የታሰሩባትን ዜጎቿን ማስፈታት እና ኢራን ደግሞ በአሜሪካ የታገደባትን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለማስለቅቅ ያስችላታል ተብሏል፡፡

ከዚህ ባሻገርም ኢራን በሩሲያ ዩክሬን ጦርነት አላት የተባለውን ተሳትፎ ማቆም፣ የዓለም የነዳጅ ዋጋን ማረጋጋት እና በመካከለኛው ምስራቅ ውጥረትን ለማርገብ ያለመም ግብ እንዳለው ተገልጿል፡፡

ድርድሩ የ2015 የአምስትዮሽ ስምምነቱን ለመመለስ ሳይሆን የአጭር ጊዜ ግቦችን ለማሳካት ያለመ ስለመሆኑ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች ገልፀዋል ተብሏል፡፡

ጊዚያዊ ስምምነቱ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የኮንግረሱን ይሁንታ መጠየቅ ሳያስፈልጋቸው ተግባራዊ ሊያደርጉት የሚችሉትም እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ይህ ድርድር ኢራን በኒውክሌር መርሃ ግብሯ ዙሪያ ያለውን መካረር ሊቀንስላት የሚችል ከመሆኑ ባሻገር ምዕራባዊያን በተባበሩት መንግስታት በኩል ማዕቀብ ለመጣል የተቀመጠውን አማራጭ እንዳይጠቀሙ ያደርጋል ሲል የአልጀዚራ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ኢራን ባለፈው ዓመት ሁለት እንግሊዛዊያንን ከእስር በመልቀቅ በእንግሊዝ መንግስት ተይዞባት የነበረ አራት መቶ ሚሊዮን ዶላር ማስለቀቋ ይታወሳል፡፡

ዋልታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *