Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

አቶ ደመቀ መኮንን ከሩዋንዳ እና ናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቪንሰንት ቢሩታ እና ከናይጄሪያ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዳሙ ኢብራሂም ጋር በኬንያ ናይሮቢ ተወያይተዋል።

ውይይቱ በሀገራቱ መካከል ያለውን በተለያዩ ዘርፎች የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ ኬንያ እየተካሄደ በሚገኘው 43ኛው የአፍሪካ ኀብረት የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ እየተሳተፉ ነው።

በኬንያ እየተካሄደ ከሚገኘው 43ኛው የአፍሪካ ኀብረት የስራ አስፈፃሚ መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር የሁለትዮሽና ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ላይ መወያየታቸውን ይታወሳል።

የአፍሪካ ኀብረት የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በነገው ዕለት እንደሚጠናቀቅ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

ኢፕድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *