Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

አቶ ደመቀ መኮንን በቻይና ያደረጉት የአምስት ቀናት ጉብኝት የሁለቱን አገራት ትብብርና ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ ነው – ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በቻይና ያደረጉት የአምስት ቀናት ጉብኝት የሁለቱን አገራት ትብብርና ወዳጅነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋገረ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ፣ የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የቻይና ጉብኝት ውጤታማ መሆኑን ገልፀዋል።

አምባሳደር መለስ ዓለም በጉብኝቱ፣ ቻይና የኢትዮጵያ ሁነኛ አጋር አገር እንደሆነች እና በቀጣይም በፖለቲካና ዲፕሎማሲ መስኮች የተሻለ ወዳጅነት ለመመስረት የሚያስችል መግባባት ላይ መደረሱን ገልፀዋል።

ከአገሪቱ ም/ፕሬዘዳንት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ከጉዋንዱንግ ግዛት አስተዳደሮች ከጉዋንዡ ከተማ ከንቲባ ጋር ጥሩ ውይይት መካሄዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

በአህጉራዊ የአፍሪካ ቀንድን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያለንን ትብብር ለማስፋትም መረዳዳት ተችሏል ብለዋል።

አምባሳደር መለስ፣ ጉዋንዡ 300 ኩባንያዎች ተሳታፊ የሆኑበት የኢንቨስትመንት ስኬታማ ውይይት መካሄዱን እና አዳዲስ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በኢንቨስትመንት ለመሰማራት ፍላጎታቸውን ማሳየታቸውን ቃል አቀባዩ ገልፀዋል።

በታላቋ ቻይና መዲና ቤጂንግ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ የተሰራውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለአገልግሎት በቅቷል።

ቃል አቀባዩ በሳምንቱ በሚኒስትር ዴኤታዎች እና ዲፕሎማቶች በኩል የተሠሩ ሥራዎችንም አብራርተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *