በጃፓን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ዳባ ደበሌ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም በጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ለሆኑት ለክቡር ታኬኦ ሞሪ በጽ/ቤታቸው በመገኘት የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ አቅርበዋል።
አምባሳደር ዳባ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት በጃፓን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ሆነው ለማገልገል በመሾማቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ሁሉን አቀፍ ግንኙት አጠናክረው ለማስቀጠል እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
የኢትዮጰያን ሰላምና ብልፅግና ለማረጋገጥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አማካኝነት ኢትዮዮጵያ ሁሉን አቀፍና የተሳካ የለውጥ ስራ ማከናወኗን ጠቅሰው፣ በቅርቡ በመንግስትና በህወሓት መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት በጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
አምባሳደሩ ጃፓን እስካሁን ላደረገችው አስተዋፅኮ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ በቀጣይ በዓለማቀፍ ተቋማት በኩል እንዲሁም በተናጠል ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የልማት እና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል።
ምክትል ምኒስትሩ በበኩላቸው ለአምባሳደሩ ቆይታቸው ስኬታማ እንዲሆን በመመኘት በትብብር እንደሚሰሩ ገልፀዋል። ወቅቱ አለም በተለያዩ ፈተናዎች እየተፈተነች ያለችበት ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው፣ የጋራ ርብርብ የሚጠይቅ በመሆኑ ጃፓን ከኢትዮጰያ ጋር በቅርበትና በትብበር ትሰራለች ብለዋል።
ምክትል ሚኒስትሩ አክለውም በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አድንቀው፣ የሀገሪቱን የወጭና ገቢ ንግድ ሚዛን ለማመጣጠን እንዲሁም ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ስምምነቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን የጠየቁ ሲሆን ጃፓን ለተግባራዊነቱ ድጋፍ እንደምታደርግ ገልፀዋል።
ፕራይም ሚዲያ
