Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ለፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ለፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በኢዝላማባድ በአገራቱ ወቅታዊ ቀጣይ በሆኑ የግንኙት ቁልፍ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ አደረጉ፡፡

በገለፃው ላይ በንግድ እና ቢዝነስ ዘርፍ እየታየ ያለው አበረታች ግንኙነት በፖለቲካ ዘርፍ በተመሳሳይ ሊደገፍ እንደሚገባ አምባሳደር ምስጋናው አስገንዝበዋል።

ኢትዮጵያ በምጣኔ ሃብት ረገድ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ አዳጊ ሃገራት አንዷ እንደሆነች ያብራሩት አምባሳደር ምስጋኑ የፓኪስታን ባለሃብቶች ተሳትፏቸውን ይበልጥ እንዲያሳድጉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የሃገራቱን ግንኙነት በሁለትዮሽ የፓለቲካ ምክክር እና በጋራ ሚኒስትሮች ደረጃ እንዲጠናከር አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ጥሪ አቅርበዋል።

በምክክሩ ላይ ቀጠናዊ እና ሃገራዊ በሆኑ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይም ገለፃ ተደርጓል።

የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ኢትዮጵያ በኢስላማባድ ኤንምባሲዋን በመክፈቷ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ትብብር ማሳደግ ፓኪስታን ከአፍሪካ ጋር ጭምር ለሚኖራት ግንኙነት እድገት ወሳኝ መሆኑን መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

ዋልታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *