Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ኒጀር የአየር ክልሏን ለማንኛውም አይነት በረራ ዝግ አደረገች


የኒጀር ወታደራዊ ቡድን የሀገሪቱን አየር ክልል ለማንኛውም ዓይነት በረራ ዝግ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

የምእራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የኒጀር ፕሬዚዳንትን በመፈንቅ መንግስት ያነሳው ወታደራዊ ቡድን በአስቸኳይ ፕሬዚዳንቱን ወደ ስልጣናቸው እንዲመልስ ከአንድ ሳምንት በፊት አሰስቦ ነበር፡፡

በኢ-ህገ መንግስታዊ መንገድ ከፕሬዚዳንትነታቸው የተነሱት መሀመድ ባዙም ወደ መምበረ ስልጣናቸው አልተመለሱም፤ ከእገታም አልተለቀቁም፡፡

የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ አስፈላጊውን ወታደራዊ እርምጃ እወስዳለው ማለቱን ተከትሎ የኒጀር ወታደራዊ መሪ የሀገሪቱን አየር ክልል ለልተወሰነ ጊዜ ለማንኛውም ዓይነት በረራ ዝግ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

“የኒጀር ቀውስ በጦርነት ሰይሆን በድፕሎማሲ እንዲፈታ እንፈልጋለን፡፡ ወታደራዊ ቡድኑ የሰጠነውን አማራጭ በመጠቀም የፈፀመውን መፈንቅ መንግስት እንዲቀለብስ እናሰስባለን,” ብሏል የምእራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ በተወካዩ አማካኝነት፡፡

ወታደራዊ ቡድኑ በበኩሉ የኒጀር አየር ክልልን አልፎ በሚንቀሳቀስ ማንኛውም ሃይል ላይ አስፈላጊውን የአፀፋ እርምጃ እንደሚወስድ ነው ባወጣው መግለጫ መግለፁን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *