Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
ዜና ትግርኛ
0

ቻይና የብሔራዊ ደኅንነት ሥርዓቷን እና አቅሟን በተፋጠነ መንገድ እንድታዘምን ፕሬዚዳንቷ ጠየቁ


የቻይና የብሔራዊ ደኅንነት ሥርዓትን እና አቅምን ለማዘመን የተፋጠነ ጥረት እንዲደረግ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጥሪ አቀረቡ።

ሺ ጂንፒንግ ጥሪውን ያቀረቡት በ20ኛው ኮሙዩኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስር በዛሬው ዕለት በተካሄደው እና በሊቀመንበርነት በመሩት የመጀመሪያው የብሔራዊ ደኅንነት ኮሚሽን ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ የቻይና ኮሙዩኒስት ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዋና ጸሐፊ እና የማዕከላዊ ሚሊተሪ ኮሚሽን ሊቀመንበር እንዲሁም የብሔራዊ ደኅንነት ኮሚሽን ዋና ኃላፊ ናቸው።

የብሔራዊ ደኅንነትን የሚያጋጥሙትን ውስብስብ እና ፈታኝ ሁኔታዎችን በደንብ መገንዘብ እና ዋና ዋና የብሔራዊ ደኅንነት ጉዳዮችን በትክክል መረዳት እንደሚያስፈልግ ፕሬዚዳንቱ አስገንዝበዋል።

የቻይናን አዲስ የዕድገት ዘይቤ በአዲስ የፀጥታ መዋቅር ለመጠበቅ ጥረት ማድረግ እና በብሔራዊ ደኅንነት ሥራው ላይ አዳዲስ መሠረት መጣል እንደሚያስልግም ማሳሰባቸውን የዘገበው ሲጂቲኤን ነው።

ኢዜኣ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *