ሲንቄ ባንክ ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ጋር ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረመ።
ስምምነቱ ባንኩ ከቢሮው ጋር በመቀናጀት የትምህርት ዓለም ማህበረሰቡ የቁጠባ ባህልን እንዲያሳድግ ለማድረግና በባንኩ እንዲቆጠቡ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
በኦሮሚያ ከ11 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችና ከ200 ሺሕ በላይ አስተማሪዎች መኖራችውንና ቢሮውም እነዚህን ሁሉ በባንኩ እንዲቆጥቡ እንደሚሰራ አስታውቋል።
የትምህርት ዓለም ማህበረሰብን ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ጋር በመቀናጀት በቁጠባ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራም ይሰራል ተብሏል።
ዋልታ
