Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ባሉበት ሆነው ቅሬታንና አቤቱታን ማቅረብ የሚያስችል የኦንላይን አገልግሎት ስራ ላይ ዋለ

የፍትህ ሚኒስቴር ውሳኔ ያገኙ የወንጀል መዛግብት ላይ ቅሬታና አቤቱታ ያላቸው ተገልጋዮች ባሉበት ሆነው ማቅረብ የሚያስችላቸውን ኦንላይን አገልግሎት ስራ አስጀመረ፡፡

በሚኒስቴሩ የተቋም ግንባታና የሪፎርም ስራዎች ሚኒስትር ዴኤታ ኤርሚያስ የማነብርሃን (ዶ/ር) የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የወንጀል መዛግብት ውሳኔዎች ላይ ተገልጋዮች የሚኖራቸውን ቅሬታና አቤቱታ ባሉበት ሆነው በአነስተኛ ወጪ ጊዜ ቆጣቢ በሆነ መልኩ ሳይንገላቱ እንዲያቀርቡ ታስቦ ድረ ገጹ መበልጸጉን ተናግረዋል።

አገልግሎቱ ለተገልጋይ ዜጎች፣ ለዘርፉ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ስራቸውን በብዙ መልኩ እንደሚያግዝ ገልጸዋል፡፡

በቀጣይም የወንጀል ፍትህ አስተዳደሩን በዚሁ መልኩ ለማደራጀት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ጉዳይ መከታተያ ዳይሬክተር ጌቱ ታደሰ በበኩላቸው አገልግሎቱ በልደታ የሚገኙ የወንጀል ጉዳይ ዳይሬክቶሬቶች፣ በአዲስ አበባ በሚገኙ 10 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እንዲሁም በድሬዳዋና በሐዋሳ የሚገኙትን ጽ/ቤቶችን እንደሚያካትት አረጋግጠዋል፡፡

ዋልታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *