ባለፉት ዘጠኝ ወራት 3.8 ቢሊየን ዶላር በሬሚታንስ ወደ ሀገር መላኩን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት አስታወቀ።
አለም አቀፍ የሬሚታንስ ቤተሰብ ቀን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ8ተኛ ጊዜ እየተከበረ መሆኑ ነው የተገለጸው።
በመድረኩ ለቤተሰብ የሚላክ ሬሚታንስ የቤተሰቦችን ህይወት ለማሻሻል እና እንደ ሀገር ድህነትን ለመቀነስ ያለውን አስተዋፅኦ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገ ነው።
ሀዋላ ወይንም ሬሚታንስ ከሀገራቸው ወጥተው በተለያዩ አለማት የሚኖሩ ዜጎች ወደ ሀገራቸው በህጋዊ መንገድ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ገንዘብ የሚልኩበት መንገድ መሆኑም ተጠቁሟል።
በመድረኩ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሙሀመድ ኢድሪስ (ዶ/ር) ባለፉት ዘጠኝ ወራት 3.8 ቢሊየን ዶላር በሬሚታንስ ወደ ሀገር መላኩን ተናግረዋል።
ከባለፉት አራት አመታት ወዲህ ወደ ሀገር ቤት ገንዘብ የመላክ ሂደቱ መሻሻል ቢታይበትም አሁንም የሚታዩ ችግሮች እንዳሉ ተጠቁሟል፡፡
ኢትዮጵያ ለቤተሰብ ከሚላክ ሬሚታንስ ያላትን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባም በመድረኩ ተነስቷል።
ድወት
