Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

በ10 ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለጸ

በ2015 በጀት ዓመት 10 ወራት ከወጪ ንግድ 2 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ገቢው በ10 ወራቱ ለማግኘት ከታቀደው 4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ መሆኑንም ገልጿል።

ገቢው የተለያዩ ምርቶችን በመላክ መገኘቱንና ከተገኘው አጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ ግብርና 78 ነጥብ 26 በመቶ፣ ማኑፋክቸሪንግ 11 ነጥብ 76 በመቶ፣ ስጋ እና ወተት ኢንዱስትሪ 2 ነጥብ 62 በመቶ፣ ማዕድን 6 ነጥብ 41 በመቶ እንዲሁም ኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ እና ሌሎች 3 ነጥብ 57 በመቶ ድርሻ ገቢ ማስገኘታቸውን አመልክቷል።

የወጪ ንግዱን ለማሳደግ በውል እና የኢንቨስትመንት እርሻ የለማ ምርት የግብይት መመሪያና የምርት ገበያ አሰራር ስርዓት መመሪያ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ መደረጉ ተጠቅሷል።

ኮንትሮባንድን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የቦሎቄ ምርቶች የድንበር ላይ ኮታ እንዲነሳ መደረጉም ተገልጿል።

የወጪ ንግድ ምርት አቅርቦትን በመጠን እና በጥምርታ ለማሳደግ የአሰራር ሥርዓት የመዘርጋትና የጫት ምርት የመላኪያ ዋጋ እንዲሻሻል ከጅቡቲ መንግስት ጋር በመወያየት የድጋፍና ክትትል ስራዎች መከናወናቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።

ዋልታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *