በኢትዮጵያ በፌደራል እና በክልል መንግስታት እንዲሁም በክልሎች መካከል የሚደረግ ግንኙነት ክፍተት እንዳለበት የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።
ይህ የተገለፀው የመንግስታት ግንኙነት ስርዓት መወሰኛ አዋጅ አተገባበር ላይ ምክክር እየተደረገ ባለበት ወቅት ነው።
የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ስዩም መስፍን፣ በኢትዮጵያ በፌደራል እና በክልል መንግስታት እንዲሁም በክልሎች መካከል የሚደረግ ግንኙነት ክፍተት አለበት ብለዋል።
በመድረኩ ችግሮችን በመለየት ቀጣይ አቅጣጫዎች እንደሚቀመጡ ተገልጿል።
ኢቢሲ
