Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

በጎንደር የአርሶአደሮች አመጽ ዛሬም ተባብሶ መቀጠሉ ተገለጸ

በጎንደር የአርሶ አደሮች አመጽ እንደቀጠለ በቦታው የሚገኙ የመረጃ ቲቪ ምንጮች ገለጹ። የአማራው ህዝብ የትግል አድባር በሆነችው ጎንደር ኦህዴድ መራሹን የኦሮሙማን አገዛዝ በቃኝ ማለት ከጀመረች ሰነባብታለች። ከሰሞኑ የአብይ አህመድ መንግስት በመላው አማራ ክልል ለአርሶአደሩ ማዳበሪያ በመከልከል እየፈጸመ የሚገኘውን የአማራን ህዝብ የማዳከም ሴራ በመቃወም በጎንደር እና አካባቢዋ የሚገኙ አርሶአደሮች ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰሙ እንደሆነ በቦታው ያሉ ምንጮች ገልጸዋል።

ይህ አመጽ በእጅጉ ያስቆጣው የኦህዴድ መራሹ የብልጽግና አገዛዝ የአርሶ አደሩን አመጽ ለማስቆም በአካባቢው የብልጽግና ካድሬ ፖሊስ አባላት በኩል ተኩስ ከፍቶ ለማስቆም ቢሞክርም በጀግናው አርሶ አደር በኩል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ተበታትኖ ተመልሷል ተብሏል።
በፓትሮል ተጭኖ አርሶ አደሩን ለመበተን የሄደው የአገዛዙ የሰራዊት አባላት በአርሶ አደሩ ከበባ ውስጥ ታፍኖ ባለበት እንዲቀር እንደተደረገም ነው የተገለጸው።

አርሶአደሮቹ ከባህር ዳር ሀሙሲት እስቴይ ስማዳ የሚወስደውን የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ በመዝጋት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። አገዛዙ ፋኖን አውግዛችሁ መንግስትን እና የመንግስትን ወታደሮች ከደገፋችሁ ነው ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ የሚሰጣችሁ በማለት በአርሶአደሩ ላይ ከፍተኛ ጫና ቢያሳድርም ሳይሳካለት ቀርቷል ነው ያሉት ምንጮቻችን።

መረጃ ቲቪ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *