Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

በጅማ ከተማ ሁለት ትላልቅ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች እየተገነቡ ነው



በጅማ ከተማ ሁለት ትላልቅ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች እየተገነቡ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡

የጅማ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዋሴ ግርማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ፕሮጀክቶቹ የሚገነቡት ከተማዋን አቋርጦ በሚያልፈው አዌቱ ወንዝ ላይ ነው፡፡ አዌቱ ፔይስትሪ ፕሮጀክት ለሦስት ዓመት ያህል እየተገነባ ያለ ሲሆን ፕሮጀክቱ ብዙ ጥቅም እንደሚሰጥ ታስቦ የተጀመረ ነው፡፡

የአዌቱ ወንዝ ከዚህ ቀደም በኅብረተሰቡ ችግር ፈጣሪ ተደርጎ የሚወሰድ የነበረና በክረምት ቆሻሻን ይዞ በመምጣት ሰዎችን ከማፈናቀል አልፎ ለተለያዩ በሽታዎች ሲዳርጋቸው የቆየ ወንዝ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባው፤ የኅብረተሰቡን ችግር ለመቅረፍ እና በሃገር አቀፍ ደረጃ እየተገነባ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶች ሌጋሲን ለማስቀጠል ታስቦ እየለማ ያለ ፕሮጀክት ነው ብለዋል፡፡

እንደ ምክትል ከንቲባው ገለጻ፤ የአዌቱ ፔይስትሪ ፕሮጀክት ሁለት ዙር ግንባታው የተጠናቀቀ ሲሆን አጠቃላይ ግንባታው 400 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ይሆናል፡፡ ግንባታው በከተማ አስተዳደሩና በተለያዩ ድርጅቶች ድጋፍ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ኢፕድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *