Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

በዶ/ር ነገሬ ሌንጮ የተመራ የኢ/ያ የህዝብ ተወካዮቾ ምክርቤት የሰው ሃብት ልማት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ዛሬ 9/8/2016 ዓ/ም በመቐለ ዩኒቨርስቲ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

በዶ/ር ነገሬ ሌንጮ የተመራ የኢ/ያ የህዝብ ተወካዮቾ ምክርቤት የሰው ሃብት ልማት ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ዛሬ 9/8/2016 ዓ/ም በመቐለ ዩኒቨርስቲ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።
የቋሚ ኮሚቴው ከመቐለ ዩኒቨርስቲ ማናጅመንት ኣመራርና ሰራተኞች ሰፊ ውይይት አካሄደዋል። ለቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢውና ኣባላቱ ተቀብለው የእንኳን ደህና መጣቹሁ ንግግር ያደረጉት የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝደንት ደ/ር ፋና ሓጎስ በዚህ ወሳኝ ወቅት ላደረጉት ጉብኝት ምስጋናቸውን ኣቅርበዋል። እንዲሁም ዩኒቨርስቲው ከጦርነቱ በፊትና ከጦርነቱ ባኋላ ያለው ሁኔታ የሚያመላክት ሪፖርት በ መቐለ ዩኒቨርስቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝደንት በደ/ር እያሱ ያዘው የቀረበ ሲሆን፤ በተጨማሪም ደ/ር ፋና ሓጎስ ያለው የበጀትእጥረት ፣የትምህርት ጥራት ግብኣት አጥረት፣ ያለፈው የ17 ወራት ያልተከፈለ የሰራተኛ ደሞዝ፣ ከተማሪዎች እየቀረቡ ያሉ ጥያቄዎች እና ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ያለበት ሁኔታ ትኩረት ሰጥተው ያለው ችግር ለቋሚ ኮሚቴው ኣባላት ኣስረድተዋል።
ከዩኒቨርሲቲያችን ሲንየር ስታፍና በተለያዩ የአመራር እርከን ያሉት ሰራተኞች ጋር በተደረገው ውይይትም ተሳታፊዎችም የቋሚ ኮሚቴው አባላት ችግሮቹን ተረድተው ችግሮቹን ለመፍታት የራሳቸው ኣስተዋፅኦ ያደርጉ ዘንድ ተማፅነዋል። በወቅቱ በተሳታፊዎቹ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ደ/ር ነገሬ ሌንጮ የመጡበት ኣላማ በዩኒቨርሲቲው ያለው ችግር ተረድተው ወደ ሚመለከተው አካል ኣድርሰው መፍትሄ ማበጀት እንደሆነ ገልፀው፤ እንደ የህዝብ ተወካዮችና የቋሚ ኮሚቴው አባላትነታቸው የተነሱ ችግሮችን ከሚመለከተው ኣካል ጋር በመወያየት ችግሩ እንዲፈታ እንደሚሰሩና፤ እንደሚፈቱም እምነታቸው የላቀ መሆኑን ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *