በደቡብ ክልል ከዚህ ቀደም ለእርሻ አገልግሎት ያልዋሉ ለም መሬቶችን ለአልሚ ባለሀብቶች በመስጠት እየተካሄደ ያለው የኢንቨስትመንት ዘርፍ ተስፋ ሰጪ ውጤት ታይቶበታል ሲሉ አቶ ርስቱ ይርዳ ገለጹ፡፡
አቶ ርስቱ ይርዳ በጉራጌ ዞን እኖር ወረዳ የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ እና የአቶ ዳኜ ዳባን የግብርና ኢንቨስትመንት ስራ ጎብኝተዋል፡፡
ባለሀብቶቹ በተሰጣቸው የኢንቨስትመንት አካባቢዎች የመንገድ መሰረተ ልማት ስራዎችን በማስፋፋት እያለሙ መሆኑን አቶ ርስቱ ተናግረዋል፡፡
የኤክስፖርት ምርቶችን በስፋት በማምረት ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬን ለማስገኘት እየሰሩ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ባለሀብቶቹ በቅባት እህሎች፣ በበቆሎ ምርጥ ዘር እና በፍራፍሬ ልማት ላይ እያካሄዱ ያለው የግብርና ኢንቨስትመንት ለአካባቢው ሕብረተሰብ የስራ እድል ከመፍጠር ባለፈ የቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረግ እንዳስቻላቸውም ጠቁመዋል።
ፋና
