Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

በኦሮሚያ ክልል ከ54 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች በበጀት ዓመት እንደሚመረቁ ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ከ54 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች በበጀት ዓመት እንደሚመረቁ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ ገለጹ፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ በክልሉ በኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ በተሰሩ ስራዎች ትልቅ ስኬት መመዝገቡን ገልጸዋል።

በዘንድሮ በጀት ዓመት 29 ሺሕ 762 ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆኑ የገለጹት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በመንግስት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና እና በተጃጂላ ለሙማ የተሰሩ መሆናቸውን አመልክተዋል።

የክልሉ መንግስት ለፕሮጀክት ትልቅ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተው ከ29 ሺሕ 762 ፕሮጀክቶች ውስጥ 19 ሺሕ በላይ የሚሆኑት በዘንድሮ ዓመት የተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ዋልታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *