Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

በኦሮሚያ ክልል በ24 ቢሊየን ብር ወጪ 6 ሺህ 81 ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል

በ2015 በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል 6 ሺህ 81 ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በቢሮው የእቅድና በጀት ዝግጅት ዳይሬክተር ሃሰን እንድሪስ÷ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ደረጃውን የጠበቀ ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት መሰራቱን ተናግረዋል፡፡

በተለይም የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እና አስፈላጊ የትምህርት ግብዓቶችን ለማሟላት በቅንጅት ተሰርቷል ነው ያሉት፡፡

በዚህ መሰረት በበጀት ዓመቱ በሕዝብ ተሳትፎ 6 ሺህ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ለመገባንት ታቅዶ 6 ሺህ 81 ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ነው የገለጹት፡፡

ለግንባታው 24 ቢሊሊየን ብር ወጪ መደረጉን ጠቁመው÷ ለዚህም ባለሃብቶችን እና ሕብረተሰቡን አመስግነዋል፡፡

ግንባታቸው ከተጠናቀቁ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 5 ሺህ 955 የሚሆኑት አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን የገልፀዋል።

ፋና

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *