በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አምስት ወራት በሙስና የተጭበረበረ 653 ሚሊዮን ብር ለመንግስት መመለሱን የክልሉ ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለመገናኛ ብዙሃን በሰጠው መግለጫ አስታወቀ።
በክልሉ በአምስት ወራት 1ሺህ 495 የሙስና ጥቆማዎች መመዝገባቸውንና 1ሺህ 204 ክስ መመስረቱን ተናግረዋል።
ክስ በተመሰረተባቸው 1ሺህ 204 ግለሰቦች 4ሺህ 80 የሚሆኑ ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን የኦሮሚያ ክልል ፀረ-ሙስና ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮሚሽነር ከፊያለዉ ተፈራ አስረድተዋል ።
ክስ ተመስረቶባችዉ ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች እና ቡድኖችም ከአንድ አመት እስከ 20 አመት እስራት የተቀጡ መሆኑን ተናግረዉ በሙስና የተጭበረበረ 653 ሚሊዮን ብር ለመንግስት መመለሱንና 128 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ በባንክ መታገዱን አስረድተዋል።
በሙስና የተወሰዱ 374 ሺህ 144 ካሬ ሜትር የከተማ መሬት ለመንግሥት መመለሱን የገለፁት ኃላፊው 846ሺህ በላይ ከሬ ሜትር መሬት ላይ እገዳ መጣሉን ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በገጠር 857ሺህ ሄክታር መሬት ለመንግስት መመለሱን ተናግረዉ 538 ሺህ በኢንቨስትመንት ስም የተወሰደ የከተማ መሬት ለመንግስት መመለሱን ገልጸዋል።
በሙስና የተሰሩ 400 ህንፃዎች ለመንግሥት መመለሳችዉ የተገለፀ ሲሆን 33 ቪላ ቤቶች እና 8 ፎቆች በህግ ታግደዋል ብለዋል።
ኮሚሽኑ በሁሉም ዞኖችና የክልሉ ከተሞች ኮሚቴ በማቋቋም ጠንካራ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን አመላክቷል።
ምንጭ፡ ዋልታ
