በአፍሪካ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን በፍትሐዊነት መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
ውይይቱ እየተካሄደ ያለው “የእኩል ምክንያታዊ የድንበር ተፋሰስ ወንዞች ተጠቃሚነት ለአፍሪካ ብልጽግና ወሳኝ ነው “በሚል መሪ ሀሳብ ነው።
በመድረኩ ላይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እንዲሁም ከናይል ተፋሰስ አገራት እና የተለያዩ የአፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተገኝተዋል።
መድረኩ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን አላማውም የድንበር ተሻጋሪ ውሃዎችን ምክንያታዊ እና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የመጠቀም ጉዳይን እውን ማድረግ በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ዋልታ
