Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

በአገርአቀፍ ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያው ዙር ኦሬንቴሽን በመሰጠት ላይ ነው።ዘንድሮ በአገርአቀፍ ለሚካሄደው የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና በአንደኛ ዙር ለሚፈተኑት 11,362 ተማሪዎች ዛሬ ሰኞ ሐምሌ1/2016 ኦሬንቴሽን እየተሰጠ ይገኛል። እነዚህ የአንደኛ ዙር ተፈታኞች ከነገ ማክሰኞ ሐምሌ 2/2016 ዓም ጀምሮ ለፈተና የሚቀመጡ ይሆናል።እንዲሁም በሁለተኛ ዙር የሚፈተኑት 8404 ተማሪዎች የሚቀጥለው ሰኞ ኦሬንቴሽን ተሰጥቶአቸው ማክሰኞ ሐምሌ 9/2016 ጀምሮ ለፈተና እንደሚቀመጡ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክስ ፕሮግራም ዳይሬክተር እና የመርኃ ግብሩ አስተባባሪ ዶ/ር ጎይትኦም ገብረዮሃንስ አስታውቀዋል።በሁለቱም ዙር በዋና ግቢ፣ በዓዲ ሓቂ እና በ ቃላሚኖ ካምፓሶች በሚገኙ 6 የመፈተኛ ጣብያዎች በጠቅላላ 19,766 ተፈታኞች ለፈተና የሚቀመጡ ሲሆን፤ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ከ500 በላይ ፈታኞች እንደሚሳተፉም ዶ/ር ጎይትኦም ጨምረው ገልፀዋል።ማሳሰቢያ:-ነገ ማክሰኞ የሚጀመረውን ፈተና ከነገወድያ እንደሆነ እየተወራ እንዳለ መረጃ ደርሶናል። ሆኖም ይህ ከእውነት የራቀ አልቧልታ በመሆኑ፤ የአንደኛ ዙር ፈተና ነገ እንደሚጀምር በጥብቅ እናሳውቃለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *