Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

በአየር ንብረት ለውጥ እና አረንጓዴ አሻራ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሄደ

በአየር ንብረት ለውጥና አረንጓዴ አሻራ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በአዲስ አበባ ተካሄደ።

“የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎችን በአረንጓዴ አሻራ መዋጋት” በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደውን ውይይት የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት በጋራ ማዘጋጀቸው ተገልጿል።

በውይይቱ በዘርፉ የዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች በመነሳት የአየር ንብረት ለውጥ እያሳደረ ያለው ተፅዕኖ ላይ የመፍትሄ ሃሳቦች ተነስቷል።

በመድረኩ የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ተሞክሮ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ለቀጣናዊ ሰላም እና ደህንነት እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ከባለድርሻ አካላት ባሻገር የማህበረሰቡ እና የመገናኛ ብዙኃን ሚናን የተመለከቱ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በውይይቱ ላይ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማትና ምሁራን፣ የዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

ዋልታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *