የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአብርሆት ቤተ መጻህፍት የዲጂታላይዚሽን አገልግሎት ሥራ ማስጀመራቸውን ገለጹ።
ቤተ መጻህፍቱ አሁን በሚሰጠው አገልግሎት በአማካይ በቀን ከ15 ሺሕ በላይ አንባቢዎችን የሚያስተናግድ ሲሆን ዛሬ በተጀመረው እና 80 ሺሕ መጻህፍት ዲጂታል በተደረጉበት አገልግሎት ከእጥፍ በላይ አንባቢዎችን መድረስ ያስችላል ብለዋል።
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መረጃ “ትውልዱ የሚያነብበት ስፍራ በማጣቱ እንጂ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት በንባብ ራሱን ለማነጽ የሚተጋ መሆኑን በማየታችን ተጨማሪ አዳዲስ ቤተ መጻህፍት በየክፍለ ከተሞቻችን እየገነባን የተጠናቀቁትንም በቁሳቁስ እንዲሟሉ በማድረግ አንባቢ እና ምክንያታዊ ትውልድ ማፍራታችንን እንቀጥላለን” ሲሉም አክለዋል።
፡
