የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ጽህፈት ቤት የዲሞክራሲ ስሰዓት ግንባታ ማስተባበርያ ፅ/ቤት በትግራይ ክልል በጦርነቱ ለተጎዱ ትምህርት ቤቶች መልሶ ግንባታ ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
ጽህፈት ቤቱ ከከተማው ወጣቶችና ነዋሪዎችን በማስተባበር ያሰባሰበ ሲሆን ድጋፉ የነገዋን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት አጋዥ እንደሆነም ነው የተገለጸው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሞገስ ባልቻ እንደገለፁት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በሚችለው ሁሉ ድጋፍ ካደረገ የሚፈለገውን የተጠናከረ ወንድማማችነትና እና አንድነትን እውን ማድረግ እንችላለን ነው ብለዋል።
ድጋፉን የትግራይ ወጣቶች ማህበር የአዲስ አበባ ተወካዮች ተረክበውታል።
የተገኘውን ሰላም ለማገናከር እና የወወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት ሁሉም መተባበር እንዳለበት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዋልታ
