በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ዙሪያ ሲካሄድ የቆዩ የውይይት መድረኮች በስኬት መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡
የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ውይይቱን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት “በነበረው የአመራር ውይይት ወዶ እና ፈቅዶ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የመረጠንን ህዝብ ዝቅ ብለን በተጨማሪ ትጋት እና መሰጠት ለማገልገል የሚያስችል አቅም እና ጉልበት ሰንቀናል” ብለዋል፡፡
ፕሮግራሙን በማስተባበርና በመምራት የተሳተፋችሁ በሙሉ በብልፅግና ፓርቲ አመራር እና አባላት ስም ልባዊ ምስጋናችንን ማቅረብ እንወዳለን ሲሉም አክለዋል፡፡
ዋልታ
