የቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ናዚ ጀርመንን ያሸነፈችበትን 78ኛ ዓመት የድል ቀን በሞስኮ እየተከበረ ይገኛል።
ፕሬዚዳንት ፑቲን በድል ቀን አከባበሩ ላይ ዓለም “ወሳኝ የለውጥ ጊዜ ላይ ትገኛለች” ያሉ ሲሆን ምዕራቡ ዓለም በሩሲያ ላይ በይፋ ጦርነት ከፍቷል ብለዋል።
ፑቲን ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የገባችበት ጦርነት የናዚዝም እሳቤ ትግል እና ሉዓላዊነትን የማስጠበቅ መሆኑንም በንግግራቸው አስምረውበታል።
በድል ቀን አከባበር ስነ ስርዓቱ ላይ የወታደራዊ ሰልፍ ትርዒት የታየ ሲሆን በሰልፉ እግረኛ ወታደሮች ፣ ታንኮች እና ሚሳኤሎች ታይተዋል።
ሀገሪቱ፣ ይህ ዓመታዊ የድል ቀን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሶቪየት ህብረት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀችውን ድል ለማስታወስ የምታከብረው የድል በዓል ነው።
ምንጭ፡ ኢዜኣ
