Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

በማክሰኝት ከተማ ስድስት የመንግስት የፀጥታ ኋይሎች መገደላቸው ተረጋገጠ።

ከጎንደር ከተማ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ማክሰኝት ከተማ፤ ረቡዕ ሐምሌ 12/2015 ዓ.ም ከምሽቱ 11 ሰዓት ጀምሮ በአገዛዙ ወታደሮች እና በፋኖ መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሦስት ፖሊስና ሦስት ሚሊሻ በድምሩ ስድስት የአገዛዙ የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም አንድ ነዋሪ መገደላቸውን መረጃ ቲቪ ከነዋሪዎች አረጋግጧል።

የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊበልጥ እንደሚችል የተጠቆመ ሲሆን፤ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የጸጥታ አካላት፣ የፋኖ አባላትና ነዋሪዎች ቆስለው ወደ ጎንደር ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል መወሰዳቸው ተገልጿል።

ባለፈው ሰኞ ሐምሌ 10/2015 በማክሰኝት ከተማ ፖሊስ ጣቢያ የአንድ የፋኖ አመራር ታሰሮ የተለቀቀ ቢሆንም፤ የጦር መሳሪያው በአገዛዙ ኃይሎች መነጠቁን ተከተሎ “የፋኖውን የጦር መሳሪያ መልሱ” በሚል ከከተማዋ በቅርብ እርቀት ረቡዕ ዕለት ሌሊቱን ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ሲካሄድ ማደሩን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በዚህም በማክሰኝት ከተማ የሚገኙ ኹሉም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች፣ ሱቆች፣ ሆቴሎች እና ባንኮች ዝግ መሆናቸውን መረዳት ተችሏል።

በአካባቢው ከሐምሌ 10/2015 ጀምሮ በአገዛዙ ወታደሮች እና በፋኖ መካከል ነግሶ በነበረው ውጥረት ረቡዕ ማታ ከተደረገው የተኩስ ልውውጥ በኋላ መቆሙንም ነዋሪዎቹ አክለዋል፡፡

በተጨማሪም በትናንትናው ዕለት ከቀኑ አምስት ሰዓት አካባቢ በጎንደር ከተማ ከዞኑ አስተዳደር እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢሮ አጠገብ አንድ የመንግሥት የሥራ ኃላፊ ባለታወቁ ኃይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸው ተሰምቷል።

Mereja.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *