Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!


Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

ስቶክሆልም፤ የአቶም ጦር መሳርያ ምርት እየጨመረ ነዉ

የዓለማችን የኒውክሌር መሳሪያ ባለቤት ሃገራት የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቻቸውን እያጠናከሩ መሆኑን ስቶክሆልም ስዊድን የሚገኘዉ ዓለም አቀፉ የሰላም ምርምር ተቋም ገለፀ። ተቋሙ ይፋ ባደረገዉ ዓመታዊ መግለጫ፤ በዓለም ላይ በሚገኙ በወታደራዊ ክምችቶች ውስጥ ጥቅም ላይ ሊዉሉ የሚችሉ የኑክሌር የጦር መሣሪያዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት በቁጥር ጨምሯል ብሏል።

የዓለማችን የኒውክሌር መሳሪያ ባለቤት ሃገራት የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቻቸውን እያጠናከሩ መሆኑን ስቶክሆልም ስዊድን የሚገኘዉ ዓለም አቀፉ የሰላም ምርምር ተቋም ገለፀ። ተቋሙ ዛሬ ይፋ ባደረገዉ ዓመታዊ መግለጫ እንዳስቀመጠዉ በዓለም ላይ በሚገኙ በወታደራዊ ክምችቶች ውስጥ ጥቅም ላይ ሊዉሉ የሚችሉ የኑክሌር የጦር መሣሪያዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት በቁጥር ጨምሯል ብሏል። በሌላ በኩል በዋና ዋናዎቹ የኑክሌር ጦር መሳር  ባለቤት ሃገራት መካከል የሚታየዉ የመግባባት፤ የግንኙነት እና የሐሳብ የመለዋወጥ እንቅስቃሴ ከበርካታ አሥርተ ዓመታት ወዲህ በጣም ቀዝቃዛ ደረጃ ላይ የደረሰበት ነዉ ሲል ተቋሙ አሳሳቢነቱን ገልጿል። ገለልተኛ የሆነዉ ስቶክሆልም ዓለም አቀፉ የሰላም ምርምር ተቋም አደረኩት ባለዉ ግምገማ ከጎርጎረሳዉያኑ ጥር 2023 ዓ.ም ወዲህ በዓለም ሃገራት ወታደራዊ ክምችቶች ጥቅም ላይ ሊውሉ በሚችሉ 9,576 የአቶም የጦር መሣሪያዎች አሉ ሲል ግምቱን አስቀምጧል። የሰላም ተመራማሪው ተቋም ቃል በቃል እንዳስቀመጠዉ ያለንበት ጊዜ “በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እጅግ አደገኛ ከሆኑት ወቅቶች አንዱ” ነዉ ሲል ገልጿል።

dw

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *