Cyber Power Tigray Media (CPT media )

ሳይበር ፖወር ትግራይ ሚድያ – ነፃን ህዝባውን ሚድያ እዩ!

Follow us on:
አማርኛ ዜና
0

” ሠልፉ የተከለከለው ለማፈን ሳይሆን የሕዝቡ ጥያቄ በውይይት በመፈታቱ ነው ” – ኮማንድ ፖስት

በከምባታ ጠምባሮ ዞን በቡድን መንቀሳቀስና መሰብሰብን ጨምሮ ሌሎች ክልከላዎች ተጣሉ።

ማምሻውን የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት አስቸኳይ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህ መግለጫው በነገው እለት የሚካሄድ ምንም አይነት ሠላማዊ ሰልፍ የለም ብሏል።

” የሀገሪቱን ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ በተለይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተካተቱ ክልከላዎችንና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተፈፃሚነት ወሰን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነገ በዱራሜ የሚካሔድ ሰልፍ እንደማይኖር ሊታወቅ ይገባል ” ብሏል።

የሰልፉ ዓላማ ከቢሮ ቁጥር ማነስ ጋር የሚያያዝ ቢሆንም የዞኑ አስተባባሪ ኮሚቴ ከክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ባደረገው ውይይት አፋጣኝ ምላሽ እንዳገኘ በመግለጫው ጠቁሟል።

በዱራሜ ተፈቅዶ የነበረው ሠላማዊ ሠልፍ የተከለከለው ” ለማፈን ሳይሆን የሕዝቡ ጥያቄ በውይይት በመፈታቱ ነው ” ሲል የገለፀው የዞኑ ጊዜያዊ ኮመንድ ፖስት ከሰዓት ጀምሮ በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች ተከልክለዋል ያላቸውን ተግባራት አሳውቋል።

  • በቡድን መንቀሳቀስና መሰብሰብ ተገድቧል።
  • ከሰልፉ ጋር በተያየዘ ቀስቃሽ መልዕክት የያዙ አልባሳት፣ ባነሮችና ጽሑፍፎችን መጠቀም ተከልክሏል።
  • ከጀምሮ የባለ 2 እና ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተገድቧል።
  • በሁሉም አካባቢ ለአፍታም ቢሆን የንግድ ተቋማትና የመንግስት መሥሪያ ቤቶች መደበኛ ሥራ መቆም እንደሌለበት አሳስቧል።

በየአቅጣጫው በፀጥታ ኃይሎች ፍተሻ እንደሚደረግም ገልጿል።

በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለሚፈጠሩ ጥሰቶች መንግስትም ሆነ የፀጥታ ኃይል ኃላፊነት አይወስዱም ሲል ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ አሳስቧል።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን፤ ከ ‘ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ‘ የተቋማት ድልደላ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቅሬታ አለ።

የቅሬታው ምንጭ፤ በክላስተር ቢሮ ክፍፍል ላይ ዞኑ ማግኘት የሚገባውን ተቋም አላገኘም፤ ሚዛናዊ ያልሆነ የቢሮዎች ክፍፍል ነው የተደረገው የሚል ነው።

ክፍልሉ እኩል የመልማት፣ የመበልፀግና የማደግ መብትን የሚገድብ በመሆኑ እንዲታረም ነው እየተጠየቀ ያለው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ለነገ ጥዋት ከ3 – 5 ድረስ የሚቆይ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቶ ነበር፤ ሰልፉም እየተፈፀመ ያለውን ኢፍትሐዊ አሰራር ለመቃወም ሲሆን፦
👉 ፍትሕ ለተጨቆነው የከምባታ ጠምባሮ ዞን ህዝብ
👉 12 ለ 1 የክላስተር ቢሮ ሽንሸናን እናወግዛለን
👉 የዞናችን ህዝብ ያነሳው የኢ-ፍትሃዊነት ጥያቄ ሳይመለስ በክልል ምስረታ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ አካላት ህዝባችንን አይወክሉም
👉 በከምባታ ጠምባሮ ዞን ላይ እየተፈፀመብንን ያለውን ኢፍትሃዊነት አጥብቀን እቃወማለን የሚሉና ሌሎችንም መልዕክቶች ለማስተላልፈ ዝግጅቶች ተደርገው ነበር።

ይህ ሰልፍ በከተማ አስተዳደሩ እውቅና አግኝቶ ዝግጅቶች ሲደረጉ ከቆዩ በኃላ ዛሬ ፍቃዱን የሰጠው የከተማው አስተዳደር ሰልፉ መሰረዙን ይፋ አድርጓል።

ዞኑ ባወጣው መግለጫ፤ የከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴ አካላት ከደቡብ ክልል አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ቢሮዎች እንዲጨመሩ ከስምምነት ደርሰዋል ሲል ገልጿል።

ለዱራሜ ከተማ እንዲጨመሩ የተወሰኑት ቢሮዎች የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስፈፃሚ መ/ቤቶችን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በሚወጣው አዋጅ ተካትተው ከሌሎች የክላስተር ማዕከላት እኩል ሥራ እንዲጀምሩ እንደሚደረግም ነው ዞኑ ያሳወቀው።

በዚህም መነሻ ነገ ሰልፍ እንደማይደረግ ገልጿል።

የዞኑ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ምን ያህል ቢሮ እንደተጨመረ፣ የተጨመሩት ቢሮዎችስ የትኞቹ እንደሆኑ በግልፅ የሰጠው መረጃ የለም።

@tikvahethiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *